Trendings

Getenesh Gebeyehu

ፕሬዚዳንት ታዬ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ21 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ መገኘቱን ገለጹ

በ2016 በጀት ዓመት በተለያዩ መስኮች ከ21 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ መገኘቱን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡ በዚሁ ወቅት ፕሬዚዳንት ታዬ ለሁለቱ የፌዴራል መንግሥት ምክር ቤቶች ዓመታዊ ሥራቸውን መጀመራቸውን በማብሰር የፌዴራል መንግሥቱን ዓመታዊ ዕቅድ አቅርበዋል፡፡ በንግግራቸውም አጠቃላይ…

Read More

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በዩኒሴፍ ፕሮግራም ገንዘብ ድጋፍ በተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ አፈጻጸም ተመዝግቧል፦ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የዩኒሰፍ ፕሮግራም አፈጻጸም በቦንጋ ከተማ ገምግሟል። በክልሉ ዩኒሴፍ ፕሮግራም ገንዘብ ድጋፍ በስምንት ቢሮዎች እና በ17 ወረዳዎች የተለያዩ ፕሮግራሞች እየተከናወነ ይገኛል። የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ በወቅቱ እንደገለጹት በ2016 በጀት ዓመት በክልሉ በዩኒሴፍ ፕሮግራም ገንዘብ ድጋፍ በስምንት ቢሮዎችና በ17 ወረዳዎች…

Read More

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ በሁለቱ ምክር ቤቶች የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል፡-

የምትሻገር ሀገር በማይሻገር ሐሳብ እየተናጠች ቆይታለች፣ የሚታረቅና የሚታረም የፖለቲካ ልዩነት እንደማይታረቅ ተደርጎ በመሠራቱ ሀገር በማይጠራ የፖለቲካ ሳንክ እንድትንገላታ ተገዳለች፣ የፖለቲካ ወለምታዎችን ለማቅናት ስብራቶችን ለመጠገን ስንጥቃቶችን ለመድፈን ስትል ዛሬም ለነገ የታሪክ የቤት ሥራ ለማስቀመጥ የሚደረጉት ሙከራዎች የሀገራችንን ፈተና አበርትተውታል፡፡ All reactions: 44

Read More

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በአገራችን የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለውና ከህዝባችን ታሪክ፣ እሴቶች እና ማህበራዊ መስተጋብሮች ውስጥ የሚንጸባረቅና የተቆራኘ አገልግሎት እንደሆነ ታሪክ ይነግረናል፡፡

በ1996 ዓ.ም ተቀርፆ ተግባራዊ የተደረገው የወጣቶች ብሄራዊ ፖሊሲ ክፍል አምስት ላይ ወጣቶች በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ የአካባቢ ጥበቃና ማህበራዊ አገልግሎት እንቅስቃሴ ውስጥ በንቃት ተሳትፈው እራሳቸውንና ማህበረሰባቸውን ሊጠቅሙ የሚችሉባቸውን ሁኔታዎች ማመቻቸት እንደሚገባ በግልፅ ተቀምጧል፡፡ ይህንንም መሰረት በማድረግ በ2002 ዓ.ም የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በተቀናጀ አግባብ ለመምራትና ብዛት ያላቸው ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ እንዲሰማሩ ለማድረግ የሚያስችል…

Read More