በክልሉ የሚገኙ ፀጋዎችን ከቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰርና በማስደገፍ ወደ ውጤት ለመቀየር እንደሚሰራ ተገለጸ።
የኢፌዴሪ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ኢኖቬሽን እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ባለድርሻ አካላት በሣይንስ እና ቴክኖሎጂ በአዲሱ ፖሊሲ ይዘት እና ስትራቴጂ አተገባበር ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ቦንጋ ከተማ ሰጥቷል። የክልሉ ኢኖቬሽን እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛው ጋጊያብ በወቅቱ እንደገለጹት በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የተዘጋጀው ፖሊሲ እና እስትራቴጂ በክልሉ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት…
