ለስጋና እንቁላል የሚሆኑ ቴትራ የተሰኙ ምርጥ የዶሮ ዝሪያዎችን ለክልሉ ሁሉም ዞኖች ለማሰራጨት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል አስታወቀ።
የክልሉ ግብርና ቢሮ በበኩሉ ክልሉ ማዕከሉን ከመዘጋት ታድጎ ለተሻለ ውጤታማነት ማብቃቱን አስታውቋል። ከ3 አሰርት ዓመታት በላይ በዶሮ እርባታ ዘርፍ ለበርካቶች ዶሮና እንቁላል ሲያሰራጭ የነበረው የቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል በመሃሉ ባጋጠመው የአስተዳደር እና መሰል ችግሮች ለመዘጋት ደርሶ እንደነበር የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ለገሠ ሻሮ ተናግረዋል። ሆኖም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከተዋቀረ ወዲህ ለማዕከሉ በሰጠው ልዩ…
