ለኑሮ ውድነት ምክንያት የሆነውን የዋጋ ግሽበት ዓለም አቀፋዊ ተጽዕኖ ለመቋቋም ተችሏል፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)
የኑሮ ውድነት አንዱ ምክንያት የሆነው የዋጋ ግሽበት ዓለም አቀፋዊ ችግር ቢሆንም፤ ይህን ለመቋቋም እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ ላይ ገለጸዋል። እንደ አይ ኤም ኤፍ መረጃ ባለፉት 40 ዓመታት ያልታየ የዋጋ ግሽበት ነው ዓለምን እየፈተናት ያለው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ ዓለም አቀፋዊ ችግር ነው እኛንም እየፈተነን ያለው…
