የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በቦንጋ ከተማ ስልጠና መስጠት ጀመረ::
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር በልዩ ሁኔታ ለተመረጡ ኢንተርፕራይዞችና ባለሀብቶች ለ 5 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ስልጠና በቦንጋ ከተማ መስጠት ጀምሯል። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አስፋው አበራ በዙም ባስተላለፉት መልዕክት የአሁኑ ስልጠና ከዚህ ቀደም ከነበረው የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና የተለየ መሆኑን ተናግረዋል ። ለዚህ…
