በቦንጋ ከተማ የመንገድ ዳር መብራት ሽቦ የሰረቀ ተከሳሽ እና የተሰረቀ ሽቦዎችን ከሌባ የገዛ አንድ ግለሰብ በእስራትና በገንዘብ መቀጣታቸዉን በካፋ ዞን ፍትህ መምሪያ አስታወቀ
ወንጀሉ የተፈጸመው በካፋ ዞን በቦንጋ ከተማ አስተዳደር ጥር 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከንጋቱ 12:00 ሰዓት በዩንቨርስቲ ቀጠና አበቺ መንደር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን ወንጀሉን የፈፀሙት ታረቀኝ ቆጭቶና ታምራት ወ/ማሪያም መሆናቸዉን የገለፁት በካፋ ዞን ፍትህ መምሪያ የታክስና ኢኮኖሚ ነክ ወንጀሎች ዐቃቤ ህግ አንዷአለም አሰፋ ናቸዉ። እንደ ዐቃቤ ህግ አንዷአለም ገለፃ ተከሳሽ ታረቀኝ ቆጭቶ የተባለው በተጠቀሰው ቀን…
