ህዝቡን ለልማት ለማነሳሳትና ሀገራዊ አንድነትን ለመፍጠር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት ሚና ከፍተኛ መሆኑን የካፋ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አጥናፉ ኃይሌ ተናገሩ።
“የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና ለሁለንተናዊ ብልፅግና!”በሚል መሪ ቃል በካፋ ዞን የሚገኙ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው። በኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ውስጥ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሚና እና ቀጣይ አቅጣጫዎች በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን ሀገራዊ ሰነድ በካፋ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳሙ እሸቱ እየቀረበ ሲሆን በተሳታፊዎች ውይይት እንደሚደረግ…
