የረዥም ጊዜ ጥያቄ የነበረው “የኔትወርክ አገልግሎት” ምላሽ በማግኘቱ መደሰታቸውን የኮይሻ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ

የዘመናት ጥያቄያቸው የሆነው የኔትወርክ አገልግሎት ምላሽ በማግኘቱ መደሰታቸውን የኮንታ ዞን የኮንታ ኮይሻ ወረዳ የኮይሻ ከተማ ነዋሪዎች ገልፀዋል። የወረዳዉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ያነጋገራቸዉ የከተማዋ ነዋሪዎች በአካባቢው በ21ኛው ክፍሌ ዘመን የኔትወርክና መብራት አገልግሎት አለመኖሩ የዘውትር ጥያቄያቸው እንደነበረና በውስጣቸው ቅሬታ ፈጥሮ የቆየ መሆኑንም ተናግረዋል። በአካባቢው ኔትወርክ ባለመኖሩ የተለያዩ አገልግሎቶች ተጠቃሚ ሳይሆኑ መቆየታቸውን የገለፁት የከተማዋ ነዋሪዎች ለአብነት የባንክ አገልግሎትን…

Read More

20ኛው የዓለም የሥራ ድርጅት አህጉራዊ ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

20ኛው የዓለም የሥራ ድርጅት አህጉራዊ ኮንፍረንስ ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ-ስርዓት በአፍሪካ ኅብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ኮንፈሰንሱ “የማይበገር ማህበረሰብ እና ጤናማ አካባቢ፤ የሰው ኃይልን በብዛት የሚጠቀሙ የኢንቨስትመንት ፕሮግራም አካሄዶች” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው። ኮንፈሰንሱ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ጨምሮ የአለም የቴክኖሎጂ እድገት፣ ሰላምና ጸጥታ፣ የሀገራት የንግድ ፖሊሲዎች እና የአየር ንብረት ለውጥ በሰራተኞች ደህንነት እና የሥራ…

Read More

የማዕድን ሀብት ስራ ላይ የተሰማሩ ማህበራትና ድርጅቶች የአካባቢ ጥበቃና የማህበራዊ ደህንነት ህጎችን ተፈጻሚ ማድረግ እንዳለባቸው ተገለጸ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የደን፣ አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለዉጥ ቢሮ በክልሉ በተለያዩ የማዕድን ሀብት ያላቸው አካባቢዎች ላይ ህጋዊ ፈቃድ ወስደው ማዕድን ስራ ላይ የተሰማሩ ማህበራትና ድርጅቶች በገቡት ውል መሠረት የአካባቢ ጥበቃና የማህበራዊ ደህንነት ህጎች ተፈጻሚነት ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የቢሮ ኃላፊው ዶክተር ኢንጂር አስራት…

Read More

በሀገር በቀል መፍትሄዎች ችግሮችን ለመፍታት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል – አቶ አደም ፋራህ

ችግሮችን በሀገር በቀል መፍትሄዎች ለመፍታት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ፡፡ በምግብ ራስን ለመቻል የተካሄዱ ጥረቶች እና የተገኙ ልምዶች የሚገመግምበት መድረክ በጅማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ አቶ አደም ፋራህ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ ያላትን መሬት እና የሰው ኃይል አጣምራ አለመጠቀሟ…

Read More

በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ያሉትን የመልካም አስተዳድር ችግሮችን ለመቅረፍ በቦንጋ ከተማ ውይይት እየተካሄደ ነው።

‎ ‎የ2017 የከተማ ልማት ስራዎች የፈጻሚና አስፈጻሚዎች የአፈጻጸም ሂደት በጥንካሬና በጉድለት በሚያሳይ ግምገማዎች እና በቀጣይ የማስፈጸሚያ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው። ‎ ‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ልዩ ረዳት አቶ አለማየሁ አይበራ በመድረኩ እንደገለጹት በብልጽግና ፓርቲ የሚመራ መንግስት ለከተሞች ልማት ከምንጊዜውም በላይ በፖሊሲም ሆነ በተግባር ትኩረት ሰጥቶ እየተገበረ ይገኛል ብለዋል። ‎…

Read More

ቆይታ ከእኛ ጋር!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በበጀት ዓመቱ ለተቋሙ የተሰጡ አበይት ተግባራትን የዕቅድ አካል በማድረግ ባለፉት 9 ወራት ስራዎችን ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ሲሰራ ቆይቷል ፡፡ ቢሮው ከሚሰራቸው አበይት ተግባራት አንዱ በክልሉ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደረጉ ጥቃቶችን የመከላከልና የህግ ከለላ በማሰጠት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ዙሪያ ከክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ…

Read More

አፍሪካ በሀገር በቀል አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የተመራ አካታች ብልጽግና በማምጣት የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ወደ አዲስ ዘመን እየተሻገረች ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ “አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን ለአፍሪካ ብልጽግና እና ትብብር” በሚል ጭብጥ እየተካሄደ ባለው “አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ለአፍሪካ” መርሃ ግብር ላይ፥ አፍሪካ በሀገር በቀል የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የተመራ አካታች ብልጽግና በማምጣት የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ወደ አዲስ ዘመን እየተሻገረች መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው አንሰተዋል። ኢትዮጵያም በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት እና የክሂሎት ማበልጸጊያ ሥራዎች በአርዓያነት እየመራች…

Read More

የሆቴሉ ስራ መጀመር በክልሉ የኮንፈረንስ ቱሪዝምን ያሳልጣል፦ አቶ ማስረሻ በላቸው

ሌዊ ሪዞርት በቦንጋ ከተማ ያስገነባው ዘመናዊ ሆቴልና ሪዞርት የክልሉን የኮንፈረንስ ቱሪዝም የሚያሳልጥ መሆኑን ነው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በምረቃው ስነ-ስርዓት ወቅት የገለጹት። ክልሉ ለሆቴልና ኢኮ-ቱሪዝም እንቨስትመንት ምቹ አከባቢ መሆኑን የገለጹት አቶ ማስረሻ የክልሉን እምቅ የቱሪዝም ሀብት ለመጠቀም በአግልግሎት ዘርፍ የአልሚዎች ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።…

Read More

የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ እየተሻሻለ መምጣቱ ተገለጸ

በሸካ ዞን የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል የአገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ለማሻሻል የሁሉም ማህበረሰብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። የሆስፒታሉ አገልግሎት አሰጣጥ እየተሻሻለ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲፈቱም ተጠይቋል። የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ አስታወሰኝ አዴሎ እንደገለፁት ሆስፒታሉ ከአካባቢው ነዋሪዎች ባሻገር ከአጎራባች ክልሎች እና ዞኖች ለሚመጡ የማህበረሰብ ክፍሎች አገልግሎት የሚሰጥ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በቀን…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልን ምን ያህል ያውቃሉ?

የደቡብምዕራብኢትዮጵያህዝቦችክልልን ምን ያህል ያውቃሉ? ባለፉት ሁለት ሳምንታት በዚህ አምድ አጠቃላይ የክልላችንን ገጽታ የሚያሳይ ፅሁፍ እንዲሁም ከክልላችን ዞኖች አንዱየ ሆነውን የምዕራብ ኦሞዞንን ቃኝተን ለውድ አንባቢዎቻችን አድርሰናል፡፡ በዚህ ሳምንት ደግሞ ከክልላችን ዞኖች አንዱ የሆነውን የካፋ ዞንን እንቃኛለን፡፡መልካምንባብ!የካፋ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልለዊ መንግስት ከሚገኙ ስድስቱ ዞኖች አንዱ ሲሆን በ12 ወረዳዎችና በ5 ከተማ አስተዳደሮች የተዋቀረ ዞን ነዉ።…

Read More