በአንድራቻ ወረዳ በተለያዩ የግብርና ልማት ስራዎች የተሰማሩ አርሶአደሮች ውጤታማ መሆናቸውን ተናገሩ
በአንድራቻ ወረዳ ጨገቻ ቀበሌ ጉምቢ ካቻ መንደር ከሌማት ትሩፋት ተግባራት አንዱ የሆነው የማር መንደር ምልከታ ተደርጓል። በቀበሌው ትኩረት ከተሰጠባቸው የሌማት ትሩፋት ተግባራት አንዱ የማር መንደር ሲሆን ይህም ውጤታማነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን አርሶአደሮች ተናግረዋል። የሸካ ዞን ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ መምሪያ ምክትል ኃላፊና የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አረጋኸኝ…
