ቲካሻ ቤንጊ አሰባሳቢ ፣ አንድነትን ፈጣሪና ባህልና ቋንቋን ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማሸጋገር ድልድይ መሆኑን የብሔረሰቡ ተወላጆች ተናገሩ።
በዓሉ ሰላምን የማጽናት ፣ ልማትን የማረጋገጥና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን የሚያጠናክር በመሆኑ የቅድመ ዝግጅት ስራው በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አዘጋጅ ኮሚቴው ገልጿል። የሸኮ ብሔር የአዲስ ዘመን ብስራትና የምስጋና በዓል የሆነው ቲካሻ ቤንጊ ለዘመናት ተቋርጦ ከቆየበት ባለፉት 2 አመታት የብሔረሰቡ ተወላጆችና እንግዶች በተገኙበት በሸኮ ከተማ በድምቀት ተከብሯል። የብሔሩ ተወላጆች ከሆኑት ውስጥ አቶ አዲሱ በዲ ፣ ኤፌሶን ሱብሳ ፣…
