የክልሉ ሱፐርቪዥን ቡድን በሸካ ዞን ድጋፋዊ ክትትል እያደረገ ነው
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ረዳት ተጠሪ በሆኑት በአቶ በላይ ተሰማ የተመራው የክልሉ ሱፐርቪዥን ቡድን በሸካ ዞን ተገኝተው የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች ግምገማ በቴፒ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል። በቆይታቸው በዞኑ እየተሰሩ ያሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን እንዲሁም የፓርቲ ተግባራት አፈፃፀም እንደሚገመግምና የተሰሩ ተግባራትን የመስክ ምልከታ እንደሚያደርግ ተገልጿል። የቡድኑ አስተባባሪና የክልሉ የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ በላይ ተሰማ…
