ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) በ20ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል ላይ ለመታደም በሆሳዕና ከተማ አብዬ ቦርሳሞ መታሰቢያ ስታዲየም ገብተዋል፡፡
20ኛው የኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን “ዲሞክራሲያዊ መግባባት፤ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሆሳዕና ከተማ እየተከበረ ነው። በብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን ለመታደም ከመላው ሀገሪቱ ወደ ሆሳዕና ከተማ የገቡ የበዓሉ ታዳሚዎች በአብዬ ኤርሳሞ መታሰቢያ ስታዲየም ባህላዊ ትርዕታቸውን እያሳዩ ይገኛሉ፡፡
