የማሻ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አቶ አንዱአለም ጌታቸውን የማሻ ከተማ ከንቲባ አድርጎ ሾመ
የሸካ ዞን ማሻ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በማሻ ከተማ አካሂዷል ፡፡ የምክር ቤቱ ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ አሰለፈች ገዘሀኝ ምክር ቤቱ በህገ መንግስቱ በተሰጠው ስልጣን መሠረት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሲወጣ መቆየቱን ተናግረዋል ። አፈ ጉባኤዋ አክለውም የምክር ቤቱ ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮች ስኖሩ በአሰራሩ መሠረት አስቸኳይ ጉባኤ መደረጉን ገልፀዋል ።…
