በክልሉ በቂ የግብርና ምርትና ምርታማነት ማሳደግ እንዲያስችል አዳዲስ በምርምር የወጡ እሳቤዎችን ተግባራዊ ማድረግ እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማሻሻል እንደሚገባ ተመላከተ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የግብርና ቢሮ እርሻ ዘርፍ ከሥርዓተ ምግብ ማጠናከሪያ ፕሮግራም(FSPR) ጋር በመተባበር ከዞንና ከወረዳ ለተወጣጡ የግብርና ባለሙያዎች በሰብል አመራረት ፓኬጅ ላይ ያተኮረ የአሰልጣኞች ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ነው ። ስልጠናው በሰብል አመራረት ፓኬጅ ፣በዋና ዋና የብርዕና አገዳ ሰብሎች በሽታ መከላከል ፣አሲዳማ እና ኮትቻ አፈር ልማት ዘዴ፣የACC እና FPC አተገባበር፣ጽንስ ሀሳብ እና…
