ለመንገድና ድልድይ ግንባታ የዲዛይን ስራዎች ተገቢውን ትኩረት በመስጠት የፕሮጀክት ውጤታማነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተመላከተ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ የመንገዶች ባለስልጣን መስሪያ ቤት፥በክልሉ በአማካሪ ድርጅቶች የተሰሩ የመንገድ እና የድልድይ ፕሮጀክቶች ጥናትና ዲዛይን ሥራ ሪፖርት በቦንጋ ከተማ ግምግሟል። በዲዛይን ግምገማው መድረክ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር አብድዩ መኮንን ለመንገድና ድልድይ ግንባታ የዲዛይን ስራዎች ተገቢውን ትኩረት በመስጠት የፕሮጀክት ውጤታማነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተናግረዋል። የአንድን ፕሮጀክት ግንባታ ውጤታማነት ለማረጋገጥ የጥናትና ዲዛይን…
