ርዕሰ መስተዳድር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የቆንዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተመለከቱ
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የክልል፣የዞንና የወረዳዉ ከፍተኛ አመራሮች የሆስፒታሉ ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው ተመልክቷል። የገዋታ ወረዳ የቆንዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ አፈጻጸም አሁን ላይ 98 ከመቶ መድረሱን በጉብኝቱ ወቅት በተደረገው ገለጻ ማረጋገጥ ተችሏል። የሆስፒታሉ ቀሪ ሥራዎች ተጠናቆ አስፈላጊ ግብዓቶች ተሟልቶላቸው ለአገልግሎት ሲበቃ ለአራት ወረዳዎች አገልግሎት መስጠት የሚችል ነዉ። በጉብኝቱ የሆስፒታሉ…
