በክልሉ 9 ወራት 77 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፦ አቶ ግዛው ጋግያብ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ የ9 ወራት የተግባር አፈጻጸም ግምገማ አድርጓል ። ባለፉት 9 ወራቶች ከፈጻሚ ዝግጅት ጀምሮ በቢሮው የተሰጡ ተልዕኮዎችን በብቃት ለመወጣት እንዲያስችል ዘርፈ ብዙ ስራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን የቢሮ ኃላፊው አቶ ግዛው ጋግያብ ተናግረዋል ። ቢሮው በአይሲቲ እና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች በተጠናቀቀው 9 ወራቶች በዋና ዋና ተግባራት የተሻሉ ስራዎች መከናወናቸውንም ገልጸዋል ።…
