በ4 ክልሎች ለባሕላዊ ፍ/ቤቶች እውቅና የሚሰጥ አዋጅ ጸደቀ
በአራት ክልሎች ለባሕላዊ ፍርድ ቤቶች እውቅና የሚሰጥ አዋጅ መጽደቁን የፍትሕ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በፌዴራልና በክልል ፍ/ቤቶች እንዲሁም የፍትሕ ተቋማት ትራንስፎርሜሽን አተገባበር ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ የፍትሕ ሚኒስትር ሐና አርዓያስላሴ እንደገለጹት÷ ባለፉት ጊዜያት የፍትሕ ሥርዓቱን ማሻሻል የሚያስችሉ በርካታ ሪፎርሞች ተከናውነዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በአማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና ሲዳማ ክልሎች ለባሕላዊ ፍ/ቤቶች እውቅና የሚሰጥ አዋጅ መጽደቁን…
