Trendings

የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በመጪው ቅዳሜ በይፋ ይከፈታል

የ2017 ዓ-ም ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በመጪው ቅዳሜ በአዲስ አበባ በይፋ እንደሚከፈት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ኤክስፖውን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኢንዱስትሪዎች ያጋጥማቸው የነበሩ ችግሮች ደረጃ በደረጃ እንዲፈቱና የማምረት አቅማቸው እንዲጎለብት ማድረጉን አንስተዋል። ንቅናቄው የአገር ውስጥ ምርት አጠቃቀም ላይ ሰፊ ለውጦች መምጣታቸውን ገልጸዋል። 3ኛው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በመጪው ቅዳሜ ሚያዝያ…

Read More

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን በአባልነት እንድትቀላቀል አሜሪካ ድጋፍ ታደርጋለች፦የአሜሪካ የንግድ ፅ/ቤት

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን በአባልነት እንድትቀላቀል አሜሪካ ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች። ከ2025 የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም እና የዓለም ባንክ የጸደይ ስብሰባዎች ጎን ለጎን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በአሜሪካ የንግድ ፅ/ቤት የዓለም ንግድ ድርጅት እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ረዳት ተወካይ ከሆኑት ኒል ጄ ቤክ ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን በአባልነት ለመቀላቀል እያደረገች ያለውን…

Read More

በእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ውጤታማ መሆናቸውን የታርጫ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ ።

በታርጫ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ያሉ የልማት ስራዎችን ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ወጣቶቹ በተሰማሩባቸው የእንቁላል ጣይ ዶሮ በቀን ከ450 በላይ እንቁላል እያገኙ መሆናቸውን ለርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከሚገኙ ዞኖች አንዷ በሆነችሁ ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር የሌማት ትሩፋት ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። የሌማት ትሩፋት አካል የሆነው የእንቁላል ጣይ…

Read More

የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመንግስትን የአገልግሎት አሰጣጥ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴን ጨምሮ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫን ጎብኝተዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመርቆ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል። ማዕከሉ 12 ተቋማትን እና ከ41 በላይ አገልግሎትን በአንድ ህንፃ ማግኘት የሚያስችል ነው። የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ እንዲሁም የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫን…

Read More

የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ታሳቢ ያደረጉ ተግባራት እየተከናወኑ ናቸው፦ የተከበሩ አቶ መቱ አኩ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት 3ኛ ዙር 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በቴፒ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ የተከበሩ ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ መቱ አኩ ጉባኤው ያለፉትን የ9 ወራት አፈፃፀም በመገምገም ለቀጣይ በቂ ግብአት የሚወሰድበት መሆኑን ገልፀው ምክር ቤቱ ህገ መንግሥታዊ ተልዕኮውን አንግቦ የክልሉን ህዝብ መብትና ጥቅም በማስከበር ረገድ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ…

Read More

ለአመታት ተቋርጦ የነበረው የዲሪ ማሻ አስፋልት መንገድ ስራ እንደገና ሊጀመር ነው ።

ለአመታት የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ የሰነበተው የዲሪ_ማሻ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ እንደገና ወደ ስራ የማስገባት ስነስርዓት በካፋ ዞን ጊንቦ ወረዳ ይደረጋል። ይህንን ስነ _ስርዓት ለማስጀመር የኢፌዴሪ ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እና የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለማየሁ አየለ የተገኙ ሲሆን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አቀባበል አድርገውላቸዋል።…

Read More

ኢትዮጵያና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ በልማት ትብብር ላይ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት አምበሮይስ ፋዮሌ ጋር በልማትና ኢንቨስትመንት ትብብር ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል። የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ እድገት ዙሪያ ተጨባጭ አስተዋጽኦ ከማበርከት አኳያ ጉልህ ሚና ያላቸው ዘርፎች ላይ ለሚያደርገው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አቶ አህመድ ሺዴ ምስጋና አቅርበዋል። በተለይም በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ፣ ውሃ፣ የንጽህና አጠባበቅና እና…

Read More

መንግስት በፈጠራና ክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

የትምህርት፣ የቴክኖሎጂና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ከ’ African Brains’ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ኢኖቬሽን አፍሪካ 2025 ጉባኤ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል መካሄድ ጀምሯል። በጉባኤው የትምህርት፣ የቴክኖሎጂና ክህሎት ጉባኤ ላይ የአፍሪካ ሀገራት የዘርፉ ሚኒስትሮችና ልዑካን ቡድን አባላት፣ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የትምህርት አጋር ድርጅቶች፣ የግሉ ሴክተር ኢንቨስተሮች እየተሳተፉ ይገኛል። ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር…

Read More

የወጣቶች ክንፍ የ2017 ዓ.ም.የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወጣት ሰዒድ ኢብራሂም ባደረገው ንግግር፣በኢኮኖሚ ዘርፍ ወጣቶች ቁጠባን ባህል አድርገው ውጤታማ በሚሆኑባቸው ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ የተሻለ እንቅስቃሴ መደረጉን ገልጿል ። ወጣቶች የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ላይ እንዲሰማሩ ለማድረግ ትኩረት መደረጉን ጠቅሰው በተለይ ወጣቱን ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለማስገባት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን በማመቻቸት ላይ እንገኛለን…

Read More

በበጀት ዓመቱ 1 ሺህ 227 ሄክታር ማልማት የሚችሉ 11 የመስኖ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ መሆኑ ተገለጸ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ የ2017 በጀት ዓመት 9 ወራት አፈፃፀም ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን የተናገሩት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተርኢንጂነር አሸናፊ ሽብሬ የመስኖ ልማትን በማስፋፋት የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን አክለዋል። በክልሉ መንግሥት በጀትና ዘርፉን በሚደግፉ በተለያዩ ፕሮግራሞች የበጀት ድጋፍ በርካታ የመስኖ ልማት ሥራዎች እየተከናወኑ እንዳለ…

Read More