የዓድዋ ድል የኢትዮጵያውያን ጀግንነትና ድል አድራጊነት በዓለም አደባባይ ከፍ ብሎ የታየበት ገድል ነው
የዓድዋ ድል የኢትዮጵያውያን ጀግንነትና ድል አድራጊነት በዓለም አደባባይ ከፍ ብሎ የታየበት የጥቁር ህዝቦች ገድል መሆኑን የታሪክ ምሁራን ገለጹ። ዓድዋ ላይ ጀግንነትን፣ ህብረ ብሔራዊ አንድነትና የአልገዛም ባይነት ወኔን ከጦርና ጎራዴ ጋር የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታገዘውን የጣሊያን ወራሪ ጦር ድል በማድረግ የሀገራቸውን ክብርና ሉዓላዊነት አጽንተዋል። የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም…
