129ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ በቦንጋ ከተማ በአካላዊ እንቅስቃሴና ፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።
በመርሀ-ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት፥ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር የማታለም ቸኮል በአድዋ አባቶቻችን ያስመዘገቡትን ድል የአሁኑ ትውልድ በልማት መስክ መድገም አለበት ብለዋል። ከተሞች ለኑሮ ምቹ እንዲሆኑ ዘወትር በየሣምንቱ የፅዳት ዘመቻ ማድረግን ህብረተሰቡ ባህል ማድረግ እንደሚገባ ያስገነዘቡት ኢንጅነር የማታለም ንቁ ዜጋ ለልማት ወሳኝ በመሆኑ ስፓርቲዊ እንቅስቃሴ ማዘውተር ይገባል ብሏል። የቦንጋ ከተማ…
