ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ ለከተራና ጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በደማቅ ሁኔታ ለሚከበረው የከተራና ጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ሙሉ መልዕክታቸው እንደሚከተለው ቀርቧል፦ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ! ጥምቀት፣ ከሰማየ ሰማያት ወረደ፣ በባሕር መካከልም ቆመ ብለን የምናከብረው በዓል ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የሕዝቡን ችግር ለመፍታት ማድረግ ያለብንን አራት ነገሮች አስተምሮናል። እነዚህም ወደ ሕዝቡ መውረድ፣ ራስን አሳልፎ…
