#ዜና_ሹመት

አቶ ፍቅሬ አማን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ ሆነዉ ተሾሙ አቶ ፍቅሬ አማን ከጥር 07 /2017 ዓ.ም ጀምሮ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የዴሞክራሲ ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የመንግስት ዋና ተጠሪ ሆነዉ ተሹመዋል። አቶ ፍቅሬ አማን ከዚህ ቀደም የቤንች ሸኮ ዞንን በዋና አስተዳደሪነት የመሩና አሁን ከተሾሙበት የመንግስት ኃላፊነት በፊት በኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት…

Read More

የ2017 የከተራ እና የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር በቂ ዝግጅት መደረጉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

እንኳን ለ2017 ለከተራና ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን የገለፁት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰብስቤ ሻዎኖ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ የአደባባይ በአላት አንዱ የሆነዉ የከተራና የጥምቀት በዓላት ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴታቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ ፖሊስ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደስራ መገባቱን ተናግረዋል። በክልሉ በስድስቱም ዞኖች፣ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች 850 ታቦታት እንዳሉ…

Read More

ኢትዮጵያና ብራዚል በብሪክስ ማዕቀፍ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ

ኢትዮጵያና ብራዚል በብሪክስ ማዕቀፍ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን እና አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ። በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ በብሪክስ የብራዚል ዋና አስተባባሪ (ሼርፓ) አምባሳደር ኤድዋርዶ ሳቦአ ጋር ተወያይተዋል። አምባሳደር ልዑልሰገድ ከአስተባባሪው ጋር የ2025 የብሪክስ ፕሬዝዳንት በሆነችው ብራዚል የቅድሚያ ትኩረት በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል። ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው ኢትዮጵያ እና…

Read More

በፈታኝ ሁኔታዎች አመርቂ የዲፕሎማሲ ስኬቶች መመዝገባቸው ተገለጸ

በፈታኝ ሁኔታዎች አመርቂ የዲፕሎማሲ ስኬቶች ተመዝግበዋል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ገለጹ፡፡ አምባሳደር ነብያት ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ ባለፉት ስድስት ወራት በውጭ ግንኙነት የተሰሩ ዋና ዋና ሥራዎችን እና ወቅታዊ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎችን የዳሰሱ ሲሆን፤ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም በማራመድ ተጨባጭ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ትስስር የሚያጠናክሩ ተግባራት መከናወናቸውን እና…

Read More

ባለፉት 3 አመታት ህብረተሰቡ በማስተባበር የተለያዩ የመንገድ ልማት ስራዎች ተሰርተዋል።አቶ ፋጂዮ ሳፒ

በክልሉ በ3 ዓመታት ዉስጥ በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎና ከአጋር አካላት በተገኘ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ከ1ሺ ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ መስራት መቻሉን አቶ ፋጂዮ ሳፒ ተናገሩ። የ122 ኪሎ ሜትር የአዲስ መንገድ እና ጥገና ስራ በቅርቡ እንደሚጀመርም ኃላፊው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠቁመዋል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና…

Read More

በሚዛን ማዕከል የሚገኙ የክልል ሴክተር ተቋማት “ከቃል ወደ ባህል” በሚል መሪ ቃል የመሰረታዊ ድርጅት አባላት ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል።

የክልሉ ህብረት ስራ ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ቀበሌ መንገሻ ኮንፍረንሱን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት ባለፉት 6 አመታት ብልጽግና የሀገሪቱን የማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስብራቶችን በመጠገንና ወደ ተሟላ የብልጽግና ጉዞ እየተጓዘ ይገኛል ብለዋል። ብልጽግና በሀሳብ ልዕልና የሚያምን እና እንደ ሀገር ከነበርንበት ስጋት በማውጣት ወደ ሚታይና ሚጨበጥ እመርታ ያሸጋገረ ፓርቲ ነው ብለዋል። ባለፉት አመታት በበጋ መስኖ ፣ በሌማት ትሩፋት…

Read More

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ የዘወትር ተግባር ሆኖ ሊቀጥል ይገባል – አቶ አገኘሁ ተሻገር

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ በማህበረሰቡ ዘንድ መለመድ ያለበትና የዘወትር ተግባር ሆኖ ሊቀጥል እንደሚገባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለፁ። በፍትህ ሚኒስቴርና በተጠሪ ተቋማት አማካኝነት በጋምቤላ ከተማ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሰሩ አምስት የአቅመ ደካሞች ቤቶች ተጠናቀው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር በተገኙበት ዛሬ ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል። አፈ ጉባዔው በዚሁ ወቅት እንዳሉት መንግስት የህብረተሰቡን…

Read More

ትምህርት ላይ ትኩረት ሰጥተን በመስራት ትውልድ የሚያመሰግን መሆን አለብን እንጅ የታሪክ ተወቃሽ መሆን የለብንም፦ አቶ አልማው ዘውዴ

የካፋ ዞን ትምህርት መምሪያ 23ኛ የአስተዳደር ጉባኤ በተለያዩ ዝግጅት እያካሄደ ነው። እንደ ሀገር የትምህርት ሴክተሩ ላይ የገጠመውን ስብራትን ለማከም የተለያዩ ስራዎችን በመስራት በርካታ ውጤት እየተመዘገበ እንደሆነ በጉባኤዉ ላይ ተገኝተዉ መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ ገልጸዋል። የትምህርት ዉጤታማነትን ለማሻሻል በተቀናጀ…

Read More

በኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ሁለንተናዊ ስርዓተ ምግብ ለመፍጠር እየተሰራ ነው – ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)

በኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ሁለንተናዊ ስርዓተ ምግብ ለመፍጠር በጋራ እየተሰራ ነው ሲሉ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ስርዓተ-ምግብ የአየር ንብረት ለውጥ ሊያደርስ ለሚችለው ተፅዕኖ ምላሽ መስጠት ላይ ትኩረቱን ያደረገ መድረክ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)÷ ለዓለም ስጋት እየሆነ የመጣው የአየር ንብረት ለውጥ በተለይ በዜጎች የአመጋገብ ስርዓት ላይ የከፋ ተፅዕኖ እንዳያደርስ ኢትዮጵያ…

Read More

የዳዉሮ ብሔር የማንነቱ መገለጫ የሆኑ መንፈሳዊና ባህላዊ ሀብቶች የበለጠ እንዲተዋወቁ የሚያስችል ሥራ ሊሠራ እንደሚገባ በዳዉሮ ዞን በታርጫ ሂዶታ (አዳሪ) ትምህርት ቤት የሚገኙ ተማሪዎች ገለጹ

የትምህርቱ ቤቱ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች የዳዉሮ ባህል ሙዚየም ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት ከ9ኛ ተማሪዎች ውስጥ ተማሪ ሳሮን አማኑኤል እንደተናገረችው የቀድሞ አባቶች ሲገለገሉ የነበሩት ቁሳዊ ሀብቶች ተደራጅተው የተቀመጡትን መጎብኘታቸው አስደስቶታል። ተማሪ አስማማው አባይነህ በበኩሉ እኛ ይህንን የዳዉሮ ባህል ማዕከል በመጎበኘታችን ዕድለኞች ነን ሲል የተናገረ ሲሆን ቀጣይ ሙዚየሙ በተለያዩ የክፍል ደረጃ በሚገኙ ተማሪዎች እንዲጎበኝ ሊደረግ እንደሚገባም ጠይቋል። ሌላው…

Read More