የአረንጓዴ አሻራን እና የተፋሰስ ልማትን አቀናጅቶ በመተግበር በተፈጥሮ ሀብት ልማት አርዓያነት ያለው ውጤት እየተመዘገበ ነው- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
የአረንጓዴ አሻራን እና የተፋሰስ ልማትን አቀናጅቶ በመተግበር በተፈጥሮ ሀብት ልማት አርዓያነት ያለው ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የ2017 ዓ.ም ሀገራዊ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ንቅናቄን በሳይንስ ሙዚየም በይፋ አስጀምረዋል። በዓይነቱ የመጀመሪያና የንቅናቄ ማስጀመሪያ አካል የሆነ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሲምፖዚየምና ዐውደ ርዕይም ”የአፈር ሀብታችን ለብልፅግናችን’’ በሚል መሪ ሀሳብ…
