የልማት ፍሬ፤ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በንጹሕ መጠጥ ውኃ አቅርቦት የታየው ታሪካዊ እምርታ”
በሀገራችን ኢትዮጵያ የታየው ታሪካዊና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ካስገኛቸው ዘርፈ ብዙ ድሎች መካከል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መመሥረት የለውጡ ጉዞ ህያውና ተጨባጭ ፍሬ መሆኑ ይታወቃል። ይህ አዲስ ክልላዊ አደረጃጀት ለዘመናት የታፈኑ የማንነትና የልማት ጥያቄዎችን ከመመለስ ባለፈ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ በተለያዩ የልማት መስኮች አመርቂና ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን በማስመዝገብ ላይ ይገኛል። ከእነዚህም መካከል የዜጎችን መሠረታዊ የኑሮ ጥራት…
