በምርምርና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ፖሊሲ ለኢትዮጵያ ብልፅግና ፋይዳው የላቀ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

በምርምርና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ፖሊሲ ለኢትዮጵያ ብልፅግና እውን መሆን ፋይዳው የላቀ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። “መረጃ ለልህቀት፣ የፖሊሲ ሚና ለበለፀገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገር አቀፍ የፖሊሲ ቀን መድረክ ተካሂዷል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር፤ በማስረጃ ላይ የተመሠረተ የፖሊሲ ቀረጻ ለሀገር ብልፅግና ያለውን ወሳኝ ሚና አፅንዖት…

Read More

በዳውሮ ዞን የመንግሥትና የፓርቲ ሥራዎች እንዲሁም የምርጫ ሂደት ያለበት ደረጃ መገምገሙ ተገለጸ

በዳውሮ ዞን የተከናወኑ የመንግሥትና የፓርቲ ሥራዎች እንዲሁም የምርጫ ዝግጅት ያለበት ደረጃ በከፍተኛ አመራሮችና በየደረጃው በሚገኙ የሥራ ኃላፊዎች በዝርዝር ተገምግሟል። በግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ በዞኑ የተጀመሩ የመንግስት እና የፓርቲ ሥራዎች ስኬታማ መሆን የሚያስችል ስራ መሰራት እንዳለበትም ገልጸዋል። የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የመንግሥትና…

Read More

የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የሥራ ጉብኝት ክልሉ አርሶና አርብቶ አደሩን ተጠቃሚነትን ሊያረጋግጡ የሚያስችሉ የተለያዩ ኢኒሼቲቦች ፍጥነትና ጥራትን ማዕከል ባደረገ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እና የክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በምዕራብ ኦሞ ዞን መኒኢት ጎልዲያ ወረዳ ጫት ቀበሌ እየተገነባ ያለውን ሞዴል የገጠር መንደር ጎብኝተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጭነት የተጀመረው የሞዴል ገጠር መንደመር በክልሉ በፍጥነትና ጥራትን ማዕከል ባደረገ መልኩ እየተከናወነ ነው። ሞዴል የገጠር መንደር የሰውና የእንስሳትን ቤት ከመለየት አንስቶ ለመኖሪያ ቤት…

Read More

በቤንች ሸኮ ዞን የመንግስትና የፓርቲ ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው

በቤንች ሸኮ ዞን የመንግስትና የፓርቲ ተግባራት አፈፃፀም እንዲሁም የ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ግምገማ የክልል ደጋፊ አካላትና ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በዛሬው ዕለት እየተካሄደ ይገኛል። ​መድረኩን በንግግር የከፈቱት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ወቅቱ አመራሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት እንዲፈጥር የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል።…

Read More

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የሁለትዮሽ ምክክር አካሄዱ

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ማጠናከር የሚያስችል ምክክር በዋሽንግተን ዲሲ አካሂደዋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የተመራውና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ፣ የብሄራዊ ደኀንነትና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንን ያካተተ ልዑክ ከአሜሪካ አቻዎቹ ጋር ተወያይቷል። ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ያካሄዱት የሁለትዮሽ መዋቅራዊ ምክክር በሦስት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን፤…

Read More

አመራሩ የምርጫና ንቅናቄ አጀንዳዎችን በተቀመጠው አሰራር ሥርዓት መሠረት መምራትና መፈጸም ይገባል፦ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የምርጫና ሌሎች ንቅናቄ አጀንዳዎች አፈጻጸም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት ተገምግሟል። በመድረኩ ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት፤ አመራሩ የምርጫና ንቅናቄ አጀንዳዎችን በተቀመጠው አሰራር ሥርዓት መሠረት በኃላፊነት መምራትና መፈጸም እንደሚገባው አሳስበዋል። በተለይም የምርጫ ሂደቶችና ሌሎች የንቅናቄ ሥራዎች በቅንጅትና በተጠናከረ አመራር እንዲከናወኑ ሁሉም የአመራር አካላት የድርሻቸውን በብቃት እንዲወጡ ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።…

Read More

በክልሉ የሕዝቡን ችግር በማድመጥ ምላሽ የመስጠቱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልሰ በብልፅግና ፓርቲ ለሕዝብ ተወካዮችና ለክልል ምክር ቤት የቀረቡ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ጋር በቀጣይ ተልዕኮዎች ዙሪያ በቦንጋ ከተማ የተካሄደው የምክክር መድረክ ተጠናቋል። በምክክር መድረኩ ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም በመገምገምና በቀጣዩ ጊዜያት መፈጸም በሚገባቸው ተልዕኮዎች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል። የምክክሩ ተሳታፊ የሁለቱ ክልል ምክር ቤት የሕዝብ ተወካዮች ፤ የክልሉ ሕዝብ የዘመናት በክልል…

Read More

በክልሉ የሚገኘውን የተፈጥሮ ሀብት እና እምቅ አቅም ለመጠቀም የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ችሎታን ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ

የክልሉ ኢኖቬሽን እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ከቦንጋ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ፖሊሲ እና የህግ ማዕቀፎች ማስፈፀሚያ ላይ ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በቦንጋ እየተሰጠ ይገኛል። የቦንጋ ዩኒቨርስቲ አካዳሚክ ምክትል ኘሬዚዳንት ዶክተር ከለለው አዲሱ ባስተላለፉት መልዕክት ዓለም የደረሰበት የቴክኖሎጂ አቅም ደረጃ ጋር እኩል መራመድ የህሊውና ጉዳይ በመሆኑ እኩል ተወዳዳሪ ለመሆን የቴክኖሎጂ ስትራቴጂ…

Read More

በክልሉ የተጎዱ መሬቶችን የማገገምና የአካባቢ ጥበቃ ስራ በልዩ ትኩረት እየተከናወነ መኾኑ ተገለፀ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሸካ ዞን የኪ ወረዳ በአርሶ አደር መር የተፈጥሮ ሀብት ማገገሚያ ፕሮጀክት አማካኝነት የተጎዱ መሬቶችን የመንከባከብ እና የችግኝ ተከላ ተካሂዷል። የክልሉ ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና የአነስተኛ መስኖ ዳይሬክተር አቶ አሚኖ መሐመድ እንደገለጹት፤ የዚህ ንቅናቄ ዋና ዓላማ የተራቆቱ አካባቢዎችን መልሶ በደን በመሸፈን የአፈር ለምነትን ማሳደግና የአርሶ አደሩን ምርታማነት ማረጋገጥ ነው። ፕሮጀክቱ…

Read More

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር የሚደረገውን ጉዞ ማፋጠን ይጠበቅብናል፦ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በብልፅግና ፓርቲ ለሕዝብ ተወካዮችና ለክልል ምክር ቤት የቀረቡ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ጋር በቀጣይ ተልዕኮዎች ዙሪያ ክልላዊ የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ 7ኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በስኬት በማጠናቀቅ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር የሚደረገውን ጉዞ ማፋጠን ይጠበቅብናል። በክልሉ ባለፉት ዓመታት…

Read More