ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በቦንጋ ከተማ የሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶችን በመጎብኘት የአፈጻጸም ክፍተቶች እንዲታረሙ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በቦንጋ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማት፣ የማረሚያ ተቋም እና የቦንጋ ዘመናዊ መናኸሪያ የግንባታ ሂደትን በዛሬው ዕለት ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በክልሉ መንግሥት በከፍተኛ በጀት ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው የቦንጋ መናኸሪያ የመጀመሪያው ምዕራፍ የአስፋልት ንጣፍ ሥራ አሁን ላይ እየተገባደደ ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተገልጿል። ርዕሰ…
