የክልሉን የንጹህ መጠጥ ዉሃና የሳኒቴሽን ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት የውሃ ሽፋን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወን ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል-ኢንጂነር በየነ በላቸው።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት የዉሃ፣ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ በክልሉ ባሉ ስድስት ዞኖች የአስር ከተሞች የዉሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ኘሮጀክት የጥናት ዝርዝር ዲዛይን የመጨረሻ ረቂቅ ሪፖርት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቦንጋ ከተማ የውይይት መድረክ አካሂዷል። የደቡብ ምዕራብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኮረፖሬሽን በክልሉ የሚስተዋለዉን የንጹህ መጠጥ ዉሃና የሳኒቴሽን ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ የጥናትና ዲዛይን ስራዎችን ከክልሉ ዉሃ፣ማዕድንና…
