እንደ ምርጫ ባሉ ወሳኝ ሀገራዊ ሂደቶች የመገናኛ ብዙኃን ሚና እጅግ የላቀ ነው – ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ
እንደ ምርጫ ባሉ ወሳኝ ሀገራዊ ሂደቶች የመገናኛ ብዙኃን ሚና እጅግ የላቀ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ ገለጹ። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን “ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ስኬት የመገናኛ ብዙሃን ሚና” በሚል ርዕስ በጋራ ያዘጋጁት መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። መድረኩ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ኃላፊነት መሆኑን…
