በክልሉ የበዓል ፍጆታ እቃዎች ላይ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት እየተሰራ ነው
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በዓላትን ተከትሎ የሚከሰቱ የምርቶችን ዋጋ ጭማሪ ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ፡፡ የቢሮ ኃላፊ አቶ ታሪኩ አካሉ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ መጪዎቹን የገናና ጥምቀት በዓላትን ተከትሎ በምርቶች ላይ እጥረትና ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት እየተሰራ ይገኛል፡፡ ለዚህም ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ ባለው መዋቅር ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ግብረ ኃይል…
