Getenesh Gebeyehu

ያለ አገልግሎት ለዘመናት በኖረው ስፍራ ዘመን የማይሽረው ሥራ ተሠርቷል፦ ከንቲባ አዳነች::

ያለምንም አገልግሎት ለዘመናት በኖረው ስፍራ ዘመን የማይሽረው ሥራ ሠርተናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ፒያሳ የተገነባውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ መርቀዋል፡፡ ምረቃውን ተከትሎም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባደረጉት ንግግር÷ ያለምንም አገልግሎት ለዘመናት በኖረው ስፍራ ዘመን የማይሽረው ሥራ እንዲከናወንበት መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡ ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)…

Read More

የዓድዋ ድል መታሰቢያው እስካሁን ባለመገንባቱ ያስቆጫል፦-ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ::

የዓድዋ ድል ከሀገርና አኅጉር ተሻግሮ በዓለም የተስተጋባ አኩሪ ድላችን ቢሆንም ይህን በአንድ ቦታ በአግባቡ የሚገልጽ የዓድዋ ድል መታሰቢያ አለመገንባቱ የሚያስቆጭ ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡ ፕሬዚዳንት ሣኅወርቅ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የዓድዋ ድል መታሰቢያ የእኛ ብቻ ሳይሆን ለነጻነት፣ ለሕዝቦች እኩልነት ተስፋን የሰጠ ድል ነው ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ድል ይዘን እስካሁን ታሪካችንን የሚመጥን…

Read More

የሰው ልጅ የሕይወት ጉዞ በዕድልና በትግል የተሞላ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)::

የሰው ልጅ የሕይወት ጉዞ በዕድልና በትግል የተሞላ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የዓድዋ ድል መታሰቢያን መርቀዋል፡፡በምረቃው ላይ ባደረጉት ንግግርም ይህንን አስደማሚ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሌሎች የጥቁር ሕዝቦች ሀገራት ሊሠሩት ቢችሉም÷ የምኒልክ ልጅ፣ የባልቻ ልጅ፣ የገበየሁ ልጅ፣ የአሉላ አባ ነጋ ልጅ መሆን ግን አይችሉም ብለዋል፡፡ዕድል ከሌለ ትግል ብቻውን ስኬት እንደማያመጣ…

Read More

ምክር ቤቱ በሁለተኛው ቀን ውሎው የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጸደቀ::

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክርቤት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል ። ምክርቤቱ እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆች ቀርበዋል። በዚህም መሠረት የተከበሩ አቶ ንጉሴ ወ/ጊዮርጊስ የምክር ቤቱ የህግ ፣ የፍትህና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ረቂቅ አዋጆችን ለምክርቤቱ አቅርበዋል። 1.የገጠር መሬት መጠቀሚያ እና የግብርና ስራ ገቢ ግብር…

Read More

ባለፉት 6 ወራት ከ1 ሚሊየን ለሚበልጡ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)::

ባለፉት ስድስት ወራት ከ1 ሚሊየን በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ጠቅላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የሥራ ዕድል ፈጠራን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ በየዓመቱ ከፍተኛ የሆነ የሥራ ፍላጎት መኖሩን ገልፀዋል። በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት…

Read More

ለመልካም አስተዳደር ችግር መፈጠር መንስኤ የሚሆኑ አካላትን የማጥራት ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ሆነው ለመልካም አስተዳደር ችግር መፈጠር መንስኤ የሚሆኑ አካላትን የማጥራት ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደ ሲሆን በስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። የምክር ቤት አባላቱ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊያና ፖለቲካዊ መስኮች እንዲሁም ወቅታዊ ጥያቄዎችን የተመለከቱ ያቀረቡ ሲሆን…

Read More

በጋራ ለሠሩ መሪዎች ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ምሥጋና አቀረቡ::

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በባሕር ዳር ከተማ ከእርሳቸው ጋር ተገኝተው ሕዝባዊ ውይይቱን ለመሩት የሶማሌ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ እና ለመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትሩ ተሥፋዬ በልጂጌ የክብር ካባ አልብሰዋል። ርእሰ መስተዳድር አረጋ “ወንድሜ ሙስጦፌ በሶማሌ ክልል የሚኖሩ ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች እኩል ተከብረው እና ደኅንነታቸው ተጠብቆ እንዲሠሩ እና እንዲኖሩ ያስቻሉ መሪ ናቸው” ሲሉ ተናግረዋል። አማራ…

Read More

በቦስተን የኒው ባላንስ የቤት ውስጥ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይና ለሜቻ ግርማ አሸነፉ::

በቦስተን የኒው ባላንስ የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይ እና ለሜቻ ግርማ ውድድሩን በበላይነት አጠናቅቀዋል፡፡ በ1 ሺህ 500 ሜትር የተወዳደረችው ጉዳፍ ፀጋይ ርቀቱን በ3 ደቂቃ 58 ሰከንድ ከ11 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ቀዳሚ ሆናለች፡፡ በዚሁ ርቀት የ18 ዓመቷ አትሌት ብርቄ ሀየሎም 3 ደቂቃ 58 ሰከንድ ከ43 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡ ወጣቷ…

Read More

የክልሉ ምክር ቤት ጉባዔ ከጥር 30/2016 ጀምሮ ሊካሄድ ነዉ::

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክርቤት 6ኛ ዙር 3ኛ የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባዔ ከፊታችን ጥር 30/2016 እስከ የካቲት 1/2016 ዓ/ም በታርጫ ከተማ እንደሚካሄድ አስታወቀ። ጉባኤውን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የክልሉ ምክርቤት ዋና አፈ ጉባዔ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ለጉባኤው አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል ። በዚህም ለጉባኤው ተሳታፊዎች ጥሪ መተላለፉን አፈጉባዔ ወንድሙ ኩርታ…

Read More

ኢትዮጵያን ለዜጎቿ ምቹ ማድረግ የሚያስችሉ አስደናቂ የልማት ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆኑን አይተናል – ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን::

ኢትዮጵያን ለአሁኑም ይሁን ለቀጣዩ ትውልድ የተመቸች ሀገር ማድረግ የሚያስችሉ የልማትና ግንባታ ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆኑን መመልከታቸውን ወደ ሀገር ቤት የገቡ ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ተናገሩ። በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚኖሩ ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ከታህሳስ 20 ቀን 2016 እስከ መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም በሶስት ዙር ወደ ሀገር ቤት እንዲመጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። የመጀመሪያው…

Read More