Getenesh Gebeyehu

ለአቶ ደመቀ መኮንን የጀግና ሽልማት ተበረከተላቸው::

የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን የሰቆጣ ቃልኪዳን የጀግና ሽልማት ተበረከተላቸው። አቶ ደመቀ መኮንን ይህን የጀግና ሽልማት ያገኙት ከ37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ጎን ለጎን በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል እየተካሄደ ባለው የሥርዓተ ምግብ ከፍተኛ መድረክ ላይ ነው። ለሽልማቱ ያበቃቸውም ለሰቆጣ ቃልኪዳን እውን መሆንና ገቢራዊነት ላደረጉት ጥረትና ቁርጥ የአመራር ብቃት ነው ተብሏል። በተለይ ደግሞ…

Read More

ሁሉን አስተሳሳሪ ገዥ ትርክት በመገንባት ጠንካራና የበለፀገች ኢትዮጵያን አውን ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው፣ አቶ ጥላሁን ከበደ::

ሁሉን አስተሳሳሪ ገዥ ትርክት በመገንባት ጠንካራና የበለፀገች ኢትዮጵያን አውን ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ገለጹ። ህብረብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሠለምና ሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ሀሳብ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሚዛን አማን ከተማ ህዝባዊ ዉይይት ተካሂዷል። የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል…

Read More

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ላይ የሚቀመጡ ተማሪዎች ምዝገባ እየተካሄደ ነው::

በ2016 ዓ.ም በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ላይ የሚቀመጡ ተማሪዎች ምዝገባ ከየካቲት 3 ቀን ጀምሮ እየተካሄደ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል። አገልግሎቱ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የምዝገባ ሂደትን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ዘንድሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ማከናወን የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑን የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ…

Read More

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) በኢትዮጵያ የተመድ የልማት ፕሮግራም ተወካይ ጋር ተወያዩ::

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) ተወካይ ሳሙኤል ባይድ ዶው ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም በአየር ንብረት ለውጥ እና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ላይ በርካታ ሃብቶችን ማሰባሰብ እና መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡ የተጀመረውን የኢትዮጵያ ስታስቲክስ ልማት ፕሮግራም ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ገልፀዋል። በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም በተለይ…

Read More

44ኛው የአፍሪካ ሕብረት አስፈጻሚዎች መደበኛ ስብስባ ተጠናቀቀ::

44ኛው የአፍሪካ ሕብረት አስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ ዛሬ ማለዳ ተጠናቋል። ስብሰባው “ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ስርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣ የሕይወት ዘመን፣ ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት“ በሚል የአፍሪካ ሕብረት ባዘጋጀው የ2024 መሪ ሀሳብ ሲካሄድ ቆይቷል። ምክር ቤቱ ከጥር 6 እስከ 17 ቀን 2016 ዓ.ም 47ኛው የአፍሪካ ሕብረት ቋሚ…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾና የኢፌዲሪ ገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ሀዋሳ ከተማ ገቡ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾና የኢፌዲሪ ገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በነገው ዕለት በሲዳማ ክልል “ህብረብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደውን ህዝባዊ የውይይት መድረክ ለመምራት ሀዋሳ ከተማ ገብተዋል። እንግዶቹ ሀዋሳ አለም አቀፍ አየር ማረፍያ ሲደርሱ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም…

Read More

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ከሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘ::

አዲስ አበባ፦ በበጀት ዓመቱ ባለፉት ሰባት ወራት ከሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር አስታወቀ። አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ቶን ገቢና ወጪ ጭነት እንዲሁም ከ115 ሺህ በላይ መንገደኞች ማጓጓዙን ማኅበሩ ጨምሮ ገልጿል፡፡ በማኅበሩ ከፍተኛ የእቅድና የፕሮግራም አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ፍስሐ መብራህቶም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት…

Read More

ሰላም እና ልማት ለኅብረተሰቡ አስፈላጊ ስለሆኑ አንዱ ያለሌላው ሊሳካ አይችልም፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ::

በአማራ ክልል የልማት ሥራዎች ዙሪያ የሚመክር የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ውይይት በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው። በምክክር ሂደቱ ላይ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምሕረቱ እና ሌሎችም የፌዴራል መንግሥት አመራሮች ተገኝተዋል። የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ወደ ክልሉ ለመጡ…

Read More

በክልሉ በዘንድሮ በበልግ እርሻ ከ3 መቶ 20 ሺህ ሄክታር መሬት በማረስ 11.9 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዷል – አቶ ማስረሻ በላቸው::

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ የ2015/16 ምርት ዘመን የበልግ ተግባር አፈፃፀም ግምገማና የ2016/17 ምርት ዘመን የበልግ የንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በንቅናቄ መድረኩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት እንደ ክልል ተደራጅተን ወደ ስራ ከገባን ጊዜ ጀምሮ…

Read More

የ24 ዓመቱ የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት አትሌት ኬልቪን ኪፕቱም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ::

የ24 ዓመቱ የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት ኬንያዊው አትሌት ኬልቪን ኪፕቱም በመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የዓለም አትሌቲክስ አስታወቀ። ኪፕቱም ባለፈው ጥቅምት ወር ቺካጎ ውስጥ በተደረገ የማራቶን ውድድር 2:00:35 በሆነ ሰዓት በመግባት የዓለም ክብረ ወሰን መስበሩ ይታወሳል። ይኸው ክብረ ወሰን ባለፈው ሳምንት መጽደቁም ይታወቃል። አትሌቱ እና ሩዋንዳዊ አሠልጣኙ ጌርቫይስ ሐኪዚማና ሕይወታቸው ያለፈው ኤልዶሬት ካፕታጋት በተባለ…

Read More