Getenesh Gebeyehu

በአፍሪካ በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊና አካታች የትምህርት ሥርዓት በመዘርጋት አህጉራዊ ልማትና እድገት ማፋጠን ይገባል::

በአፍሪካ በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊና አካታች የትምህርት ሥርዓት በመዘርጋት አህጉራዊ ልማትና እድገትን ማፋጠን እንደሚገባ በትምህርትና ልማት ዘርፍ የሚሰሩ የተለያዩ ተቋማት ገለጹ። 37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ “ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ሥርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣ የሕይወት ዘመን፣ ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት” በሚል መሪ ሃሳብ ተካሂዷል። የሕብረቱ ጉባዔ መሪ ሃሳቡን ትምህርት…

Read More

ሴቶችን ማስተማር መብታቸውን አውቀውና አስከብረው በነጻነት እንዲኖሩ የማድረግ ጉልህ ሚና አለው -ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ::

ሴቶችን ማስተማር ተወዳዳሪ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማስቻሉም በተጨማሪ መብታቸውን አውቀውና አስከብረው በነጻነት እንዲኖሩ የማድረግ ጉልህ ሚና አለው ሲሉ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ተናገሩ፡፡ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ” እሷን አስተምሩ እና አፍሪካን ለውጡ” በሚል መሪ ቃል በ28ኛው የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች የልማት ድርጅት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡ በንግግራቸው ÷ሴቶችን ማስተማር ተወዳዳሪ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማስቻሉም በተጨማሪ…

Read More

ሰልጣኝ አብራሪዎች የኢትዮጵያን አየር ኃይል የስኬት ጉዞ የሚያስቀጥሉ ተረካቢ ትውልድ ናቸው – ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ::

ሰልጣኝ አብራሪዎች የኢትዮጵያን አየር ኃይል የድልና የስኬት ጉዞን የሚያስቀጥሉ ተረካቢ ትውልድ መሆናቸውን በመገንዘብ ሙያዊ አቅማቸውን ለማሳደግ እና በቴክኖሎጂ ራሳቸውን ለማብቃት ይበልጥ መዘጋጀት አለባቸው ሲሉ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ተናገሩ። ዋና አዛዡ በ L-39 እና በሴሲና 172 ስኳድሮኖች የሶሎ በረራን ስልጠና በሚገባ አጠናቀው ወደ ቀጣዩ ምዕረፍ የተሸጋገሩ ሰልጣኝ አብራሪዎችን በአየር ኃይል…

Read More

በአፍሪካ ሽብርተኝነት፣ ጽንፈኝነት፣ ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ የመንግሥት ለውጥ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል::

በአፍሪካ ሽብርተኝነት፣ ጽንፈኝነት፣ ግጭት፣ ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ የመንግሥት ለውጥና ሌሎችም የጸጥታ ሥጋቶች የአህጉሪቷ ፈተና ሆነው በመቀጠላቸው ዘላቂ መፍትሄ ሊበጅላቸው እንደሚገባ የአፍሪካ ኅብረት ገለጸ። የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ ሠላምና ደኅንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዴኦዬ፤ ከ37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የአህጉሪቱን የጸጥታ ጉዳዮች አስመልክተው ማምሻውን መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም፣ በአፍሪካ ሽብርተኝነት፣ ጽንፈኝነት፣ ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ የመንግሥት ለውጥ፣ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች፣…

Read More

የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት መሆኑ ተመላከተ::

37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። ጉባኤውን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ፥ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የእንግዶች ቆይታ ያማረ እንዲሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል። በሶማሊያ መንግስት በኩል የቀረበው ውንጀላ ኢትዮጵያ ለእንግዶች ያደረገችውን እንክብካቤ የማይመጥን ነው ብለዋል። ሁሉም መሪዎች ያለ ልዩነት አቀባበልና መስተንግዶ እንደተደረገላቸውም ጠቁመው፥…

Read More

37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጠናቀቀ::

37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎች በማሳለፍ ዛሬ ማለዳ ተጠናቋል። ጉባኤው “ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ስርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣ የሕይወት ዘመን፣ ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት“ ሕብረቱ ባዘጋጀው የ2024 መሪ ሀሳብ ከቅዳሜ ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቷል። በጉባኤው የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የሕብረቱ ተቋማትና አደረጃጀቶች አመራሮች ተሳትፈዋል።…

Read More

የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በመፋጠን ላይ ነው::

የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ሂደት በመፋጠን ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ገለጸ፡፡ የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንዳለ አሰፋ÷ በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡ ከነዚህ መካከል በ926 ሚሊየን ብር ወጪ እየተከናወነ የሚገኘው የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ አንዱ መሆኑን ተናግረው፤ የግንባታ ሒደቱ 54 በመቶ መድረሱን ጠቁመዋል፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች…

Read More

ኢትዮጵያ በ37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በትምህርት ዘርፍ ያስመዘገበቻቸውን ድሎች ታንጸባርቃለች::

ኢትዮጵያ በ37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በትምህርት ዘርፍ ያስመዘገበቻቸውን ድሎች እንደምታንጸባርቅ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። በጉባኤው ላይ ከአባል ሀገራቱ መሪዎች በተጨማሪ የስድስት ሀገራት መሪዎች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተመላክቷል። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ፤ በጉባኤው 49 ሀገራት እንደሚሳተፉ ይጠበቃል ብለዋል። እንዲሁም ከአባላት…

Read More

በክልሉ በሺሽንዳ እና በደካ ከተማ አስተዳደሮች ህዝባዊ ውይይት መካሄድ ተጀምሯል::

በሺሽንዳ እና በደካ ከተማ አስተዳደርሮች ከተለያዩ ማህበራዊ መሠረቶች ከተወጣጡ ማህበረሰብ ጋር ከተማ አቀፍ ውይይት እየተካሄደ ነው። ህዝባዊ ውይይቱ ምልዓተ ህዝቡ ስለአጠቃላይ ሀገራዊ ፖለቲካ ፣ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊ ና የሠላም ሁኔታ ላይ በበቂ ሁኔታ ከመንግስት ጋር በመወያየት ለመፍትሔው የጋራ ርብርብ ለማድረግ አስፈላጊ መሆኑም ተገልጿል። በውይይቱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት…

Read More

የአፍሪካ መሪዎች ሙስናን መከላከልና መቆጣጠር ላይ ጠንካራ የጋራ አቋም ሊይዙ ይገባል::

የአፍሪካ መሪዎች ሙስናን መከላከልና መቆጣጠር ላይ ጠንካራ የጋራ አቋም ሊይዙ እንደሚገባ የአፍሪካ ህብረት የሙስና መከላከል አማካሪ ቦርድ ገለጸ። የአፍሪካ ህብረት የሙስና መከላከል አማካሪ ቦርድ የስራ አመራሮች ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። የቦርዱ ሊቀመንበር ሴናቡ ዲካቴ፤ ህብረቱ እ.አ.አ በ2003 ሙስናን ለመዋጋት ያወጣው ስምምነት በአግባቡ ተግባራዊ ባለመደረጉ የሚፈለገው ውጤት አለመምጣቱን አንስተዋል። ቦርዱ የአፍሪካ ህብረት ሙስናን መከላከልና መቆጣጠር ያስችላል…

Read More