ችግሮች በተከሰቱባቸው አካባቢዎች ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ የሀገር ሽማግሌዎችና የጎሳ መሪዎች ትኩረት እንዲሰጡ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አሳሰቡ።
የመኧን አርብቶ አደር ማህበረሰብ ከኮንታና አጎራባች ህዝቦች ጋር የይቅርታና የእርቅ ስነ ስርዓት በኮይሻ ከተማ ተካሂዷል ። በህብረተሰቡ ዘንድ ዘልቆ የቆየውን ተቃርኖ ለመፍታት በመኧን ማህበረሰብ ባህላዊ የእርቅና የይቅርታ ስነስርዓት (ታራይ) በመፈጸም ተከናውኗል ። የእርቅና የይቅርታ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በመኧንና ኮንታ ኮይሻ ህብረተሰብ ዘንድ የቆየውን ቁርሾ ለመቅረፍ የክልሉ መንግስት ብርቱ…
