BLOGS
የተለያዩ አርቲስቶችና ኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የሃላላ ኬላ ሎጂን እየጎበኙ ነዉ
ከመላው ኢትዮጵያ የተወጣጡ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ተወካዮች በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ሀሳብ አመንጭነት የተገነባውን የሃላላ ኬላ ሎጂ ለመጎብኘት ወደ ዳውሮ ዞን ገቡ። የኪነጥበብ ባለሙያዎቹ ወደ ዞኑ ስደርሱ የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ፣ ለሌች የዞንና የሎማ ቦሳ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች በስፍራው ተገኝተው ደማቅ አቀባበል አድርገዋል። በአቀባበል ስነስርዓቱ፥ የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት…
‹‹‹‹‹‹ ሪፖርታዥ ››››››
የግብርና ዘርፍ ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት ውስጥ ከሚበረክተው ድርሻ አኳ ከፍተኛውን የሚሸፍንና የኢኮኖሚ መሠረት በመሆን ለማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ከፍተኛ አስተዋፅዖ የሚያበረክት የኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ ነው። የግብርናው ዘርፍ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በዘላቂነት የማሳደግ እና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግርን እውን የማድረግ ድርብርብ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል። በመሆኑም በቀጣዮቹ ዓመታት የሚኖረውን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሀገሪቱን ሕዝብ የመመገብና ሀገራዊ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ፣ በመካከለኛ…
ታዋቂ አርቲስቶችና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የተለያዩ የልማት ስራዎችን ለመመልከት ኮንታ ዞን ደርሰዋል
በሀገር ደረጃ ለ3 ተከታታይ ቀናት ከኪነጥበብ ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተደርጎ እንደ ሀገር እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን ምልከታ ለማድረግ እንደሆነ ለማድረ ያለመ መሆኑን የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ ገልጸዋል። ባለሙያዎቹ ወደ ኮንታ ዞን ኮንታ ኮይሻ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በአቀባበል ወቅት የዞን አመራር አካላትና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል። ባለሙያዎቹ በቆይታቸው…
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ማንሰራራት የተገለጠበት ብሔራዊ ሀብታችን ነው፦ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አባቶቻችን ኪሳቸውን ፈትሸው፣ እናቶቻችን መቀነታቸውን ፈትተው ጥሪት ያፈሰሱበት እንዲሁም የመከላከያ ሠራዊት አባላት መስዋዕት የሆኑለት ብሔራዊ ሀብታችን ነው ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ። የሕዳሴ ኮር ሦስተኛ ዓመት የምሥረታ በዓል “ሕዳሴን በሕዳሴ ኮር” በሚል መሪ ሐሳብ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ…
የውጭ ዜጎች የቋሚ ንብረት ባለቤትነት ረቂቅ አዋጅ ቢጸድቅ የሚያስገኘው ጠቀሜታ ምንድን ነው?
65 ዓመታትን የስቆጠረውንና የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለይዞታ መሆን እንዳይችሉ ያደረገውን አዋጅ ለማሻሻል ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱ ይታወቃል። በዚህ ረቂቅ አዋጅ ላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ውይይት እያካሄደ ነው። የፍሕ ሚኒስቴር እና የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል። አዋጁ መሻሻሉ ስለሚኖረው ጠቀሜታ…
ኢትዮጵያ በመረጃ ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ውሳኔዎችን እየሰጠች ትገኛለች – ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር)
ኢትዮጵያ በዲጂታል ስርዓት የታገዘ የግምገማ ስርዓትን በመከተል በመረጃ ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ውሳኔዎችን እየሰጠች እንደምትገኝ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) ተናገሩ። የአፍሪካ የግምገማ ማህበር 25ኛ የምስረታ በዓሉን ምክንያት ያደረገ ውይይት በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ ኢትዮጵያ ለምትተገብራቸው ፖሊሲዎችና የልማት ዕቅዶች ውጤታማነት ጠንካራ የግምገማ ስርዓት ዘርግታ እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል።…
በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከ107 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ተሰብስቧል፦ ግብርና ሚኒስቴር
በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በዘር ከተሸፈነው 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት እስካሁን ከ107 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። የግብርና ሚኒስቴር የሰብል ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ኢሳያስ ለማ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ በርካታ ተግባራት እያተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በእነዚህ ተግባራትም በግብርናው ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እየተቻለ መሆኑን ጠቁመው በስንዴ ልማት…
ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ማዕከል ያደረገ የብሔራዊነት ትርክት ለማጽናት ወጣቶች የመሪት ሚናቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አቶ ፍቅሬ አማን አሳሰቡ።
ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ማዕከል ያደረገ የብሔራዊነት ትርክት ለማጽናት ወጣቶች የመሪት ሚናቸውን አጠናክረው ማስቀጠል እንደሚገባቸው የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ተናገሩ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ለወጣቶች የአቅም ግንባታ ስልጠና በሚዛን አማን ከተማ በዛሬው ዕለት መስጠት ጀምሯል። በስልጠናው መድረክ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ብልጽግና…
ኢትዮጵያ 2ኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ታስተናግዳለች – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር 2ኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እንደምታስተናግድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡
