በክልሉ የተጀማመሩ ኢንሼቲቮችን በቁርጠኝነት በመምራት የህዝብ የልማት ተጠቃሚነት በተግባር ማረጋገጥ ይገባል።ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፤ የአስፈጻሚ ተቋማት እና የፓርቲ የተግባር አፈጻጸም ተገምግሟል። በክልሉ ለተጀማመሩ ነባር ፕሮጀክቶች ቅድሚያ በመስጠት እና እንዲጠናቀቅ በማድረግ የልማት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ነው ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) በመድረኩ ማጠቃለያ የገለጹት። የተጠናከረ የድጋፍና ክትትል ስርዓት በመዘርጋት በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በዋና ዋና ዘርፎች በክልሉ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል…
