የውስጠ ፓርቲ አንድነትን በማጠናከር የብልጽግና ፓርቲ ጉዞን እውን ለማድረግ አመራሩ እና አባሉ በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለፀ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የቴፒ ብዝሃ ማዕከል የክልል ሴክተር የብልጽግና ፓርቲ ህብረት የ2017 በጀት ዓመት 3ኛ ሩብ ዓመት የአባላት ኮንፈረንስ በቴፒ ከተማ አካሂዷል። በአባላት ኮንፈረንስ ላይ ንግግር ያደረጉት ቴፒ ብዝሃ ማዕከል የብልጽግና ፓርቲ ህብረት ሰብሳቢ አቶ ደምሴ ደንቦ የፓርቲውን አሰራሮች እና አደረጃጀቶችን በማጠናከር የውስጠ ፓርቲ አንድነትን በማጉላት ተግባራትን የመምራት…
