የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ከኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ጂማ ቅርንጫፍ ጋር በመቀናጀት በቤንች ሸኮና ሸካ ዞኖች ግማሽ ሚሊየን ብር የሚጠጋ የተበላሹና የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ምግብና መጠጦችን ማስወገዱን አስታወቀ።
ህብረተሰቡ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸውና ባዕድ ነገር የተቀየጡ ምግቦችን ሲመለከት በአቅራቢያቸው ለሚገኝ የጸጥታ አካላትና በ8284 በነጻ በመደወል ጥቆማ መስጠት እንዲተባበሩ ጥሪ ቀርቧል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ከኢትዮጵያ የምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ጂማ ቅርንጫፍ ጋር በመቀናጀት በቤንች ሸኮ እና ሸካ ዞን በምግብና መጠጥ አከፋፋዮችና የችርቻሮ ሱቆች የክትትልና የቁጥጥር ስራ መስራቱን ገልጿል። በክልሉ ጤና ቢሮ የጤናና ጤና…
