ኢትዮጵያ በኮቪድ 19 ወረርሺኝ የተጎዳውን የቱሪዝም ዘርፍ በማነቃቃት ባለፉት 5 አመታት የአለም አቀፍ ጎብኚዎቿ ቁጥር በ40 በመቶ እድገት ማሳየቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቱሪዝም ዘርፍ መረጃ አመልክቷል።
በዚህም እ.አ.አ ከ2019 ወዲህ ባስመዘገበችው የቱሪስት ፍሰት መጠን ኢትዮጵያ ከአለም ሃገራት ስድስተኛ እንዲሁም ከአፍሪካ ደግሞ ሞሮኮና ግብፅን በማስከተል ቀዳሚ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
