የአየር ወለድ ትምህርት ቤት የልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር አባላትን በአየር ወለድነት አሰልጥኖ አስመረቀ
በኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ የአየር ወለድ ትምህርት ቤት የልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር ሠልጣኞችን በአየር ወለድነት አሰልጥኖ አስመርቋል። የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ለተመራቂ የልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር አባላት የአየር ወለድ ልዩ ምልክት የሆነውን የደረት ክንፍ አልብሰዋል። የአየር ወለድ ስልጠና የወሰዱት የክፍሉ አባላት ቀደም ብለው እጅግ ፈታኝና ውስብስብ የሆነ…
