የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በመሬት ናዳና መንሸራተት ለተፈናቀሉ ወገኖች ግምቱ ግማሽ ሚሊየን ብር የሚያወጣ የምግብ እህሎች ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉ በካፋ ዞንና በቤንች ሸኮ ዞን በመሬት መንሸራተት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች እንደሚሰጥም ታውቋል። የሰብዓዊ ድጋፉን ይዘው የቀረቡት የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ በላይ አሪሶ እንደተናገሩት ግምታቸው ግማሽ ሚሊዮን የሚያወጡ የምግብ እህሎችን ለተጎጂዎች ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል ። ከአቅም በላይ በሆነ የተፈጥሮ አደጋ በመሬት መንሸራተት ሳቢያ የተፈናቀሉ ወገኖችን ባሉበት አካባቢ ቀርቦ በማጽናናት ሰብዓዊነታታቸውን…
