ስታርትአፖችን ማስተናገድ የሚያስችል ሥነ-ምሕዳር ለመገንባት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
ስታርትአፖችን በአግባቡ ማስተናገድ የሚያስችል ሥነ-ምሕዳር ለመገንባት በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡: በኢትዮጵያ የስታርትአፕ ሥነ-ምህዳርን ምቹ ለማድረግ እየተዘጋጀ ባለው ረቂቅ አዋጅ ዝርዝር ይዘት ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) እና የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ የስታርትአፕ ረቂቅ አዋጅ ለማዘጋጀት የሚያስችሉ ግብዓቶች…
