ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ በሚመክረው 10ኛው የኦራን ሴሚናር ላይ እየተሳተፈች ነው
በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው የተመራ ልዑክ በአልጄሪያ ኦራን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው 10ኛው የአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ሴሚናር ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ ላይ የሚመክረው ሴሚናሩ ከአፍሪካ ህብረት በተሰጠው ሃላፊትነት መሰረት በአህጉሪቱ ሰላምና ጸጥታን በማረጋገጥ በኩል ባለፈው አስር ዓመት የተሰሩ ስራዎችና ያጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ እየመከረ ይገኛል። ዓመታዊ ሴሚናሩ በዋናነት በአፍሪካ ሕብረት የሰላምና የጸጥታው ምክር…
