NATIONAL NEWS
መንግስትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት በማጠናከር ኢትዮጵያ በርካታ ጉዳዮችን አሳክታለች፡፡ በተለይ መንግስትና ህዝብ ተባብረው ስለሰሩ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ኢትዮጵያ 48 ቢሊየን ችግኝ ተክላለች አንዱ ችግኝ በአንድ ዶላር ቢታሰብ 48 ቢሊየን ዶላር ነው፡፡ ይህ በራስ አቅም የተፈጸም ትልቅ ስራ ነው፡፡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
የአፈር ማዳበሪያ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት ብቻ የግብርና ምርታማነትን ቢያንስ በእጥፍ ማሳደግ ይቻላል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሜጋ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፣ የማዳበሪያ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት ብቻ የግብርና ምርታማነትን ቢያንስ በእጥፍ ማሳደግ እንደሚቻል ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ በጋዝ፣ ማዳበሪያ፣ አውሮፕላን ማረፊያና ቤቶች ልማት ላይ የምንሰራው ስራ ጨዋታ ቀያሪ ነው ሲሉ ገልጸዋል። የማዳበሪያ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት ብቻ የግብርና ምርታማነትን ቢያንስ በእጥፍ ማሳደግ እንደሚቻል ገልጸው፣ ይህም በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ…
ሜጋ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ
ኢትዮጵያ ውስጥ በጋዝ፣ ማዳበሪያ፣ አውሮፕላን ማረፊያና ቤቶች ልማት ላይ የምንሰራው ስራ ጨዋታ ቀያሪ ነው። የማዳበሪያ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት ብቻ የግብርና ምርታማነትን ቢያንስ በእጥፍ ማሳደግ ይቻላል። ይህም በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ትልቅ እጥፋት ነው። ሌሎችም ሲጠናቀቁ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ይመጣል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-
2017 ዓ.ም ይቻላል ተብለው ያልታሰቡ ጉዳዮች የተከናወኑበት እና የስኬት ዓመት ነበር፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የግብርና መር ፖሊሲ ይከተል ነበር ይህንን ወደ ብዝሀ ዘርፍ ቀይረን በእጅጉ ውጤታማ ሆነናል፣ በአንድ ሴክተር ላይ ተንተርሶ መስራት ከድህነት አረንቋ ስለማያወጣን ብዝሀ ዘርፍን በመከተላችን ውጤት አምጥተናል፣ ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝም እና ቴክኖሎጂ እነዚህ አምስት ግንባር ቀደም ሴክተሮች ብዝሀ ዘርፍ ሆነው ቢመሩ የኢትዮጵያን…
ብዝሃ ዘርፍ ትብብርን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ የሰጡት ማብራሪያ
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ብዝሃ ዘርፍ እንዲሸጋገር የተነደፈው ፖሊሲ በእጅጉ ውጤታማ ሆኗል። መንግስት ከህዝብ ጋር ተሳስሮ ልማት እንዲያመጣ ግልጽ አቅጣጫ የተቀመጠውም ከለውጡ ወዲህ ነው። ለአብነትም መንግስትና ህዝብ ተሳስረው በአረንጓዴ አሻራ አማካኝነት 48 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል ችለዋል። ለዚህ ስኬት ደግሞ ከ25 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ሳይታክቱ በነጻ በየ ዓመቱ ወጥተው ችግኞችን መትከል ችለዋል። ይህም የመንግስትና ህዝብ…
የሀገራዊ ሪፎርሙ ዋና ዋና ዓላማ
የማክሮ ኢኮኖሚውን ማረቅ የንግድና የኢንሸትመንት ከባቢን ማሻሻልና ማዘመን የዘርፎችን ምርታማነትና የመወዳደር አቅማቸውን ማሳደግ የማስፈፀም አቅማችንን ማሳደግ ዘላቂ የፋይናንስ ስርዓትና ጥራት ያለው እድገት ማረጋገጥ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
በተወሰዱ ርምጃዎች የዋጋ ንረቱ ቀንሷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
በተወሰዱ የተለያዩ ርምጃዎች የዋጋ ንረቱ እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው። በማብራሪያቸውም፤ በተወሰዱ ርምጃዎች የዋጋ ንረቱ መቀነሱን ተናግረዋል። ለዚህም በምክንያያትነት የሚጠቀሱት ከአቅርቦት አንጻር በግርብርና ዘርፍ በስፋት መሠራቱ፣ የገበያ ትስስርም ቅዳሜና እሁድ ገበያዎችን በማስፋት ሻጭና ሸማችን በቀጥታ…
