Trendings

በሀገራችን የተጀመሩ ታላላቅ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን መፃኢ እድል የሚወስኑ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

በሀገራችን የተጀመሩ የጋዝ፣ የማዳበሪያ፣ የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ እና ሌሎችም ታላላቅ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን መፃኢ እድል የሚወስኑ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እያካሄደ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች እና…

Read More

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ጊዜውን ጠብቆ የሚካሄድ ይሆናል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ጊዜውን ጠብቆ የሚካሄድ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሔደ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ሲሆን በማብራሪያቸው፤ ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ከስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ የተሻለ ይሆናል ብለዋል፡፡ ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ…

Read More

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ብዝሃ-ዘርፍ እንዲሸጋገር የተነደፈው ፖሊሲ ውጤታማ ሆኗል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ብዝሃ-ዘርፍ እንዲሸጋገር የተነደፈው ፖሊሲ በእጅጉ ውጤታማ ሆኗል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ፤ መንግስት ከሕዝብ ጋር ተሳስሮ ልማት እንዲያመጣ ግልጽ አቅጣጫ የተቀመጠው ከለውጡ ወዲህ መሆኑን ገልጸው÷ ለአብነትም መንግስትና ህዝብ…

Read More

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በሚዛን አማን ከተማ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ስራ ተዘዋውረው ተመለከቱ።

‎ ‎ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በአማን ከተማና በሚዛን ከተማ በምዕራፍ ሁለት እየተሰራ ያለውን የኮሪደር ልማት ስራ ምልከታ አድርገዋል። ‎ ‎በጉብኝቱ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማንን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል እንዲሁም የዞንና የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል። ‎ ‎በሚዛን አማን ከተማ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት…

Read More

የኢትዮጵያን ሕልም አናሰርቅም፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የኢትዮጵያን ሕልም ማንም ሰው ቢያወጣው እና ቢያወርደው እኛ ግን የኢትዮጵያን ሕልም አናሰርቅም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ ሕልማችን የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ማድረግ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዚህ ጉዳያችን ግራ ቀኝ አንልም ሲሉ ነው የገለጹት፡፡ በከፍተኛ ኩራት ልንገልጸው የምንፈልገው እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2032 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከፍታ ከአፍሪካ ቢያንስ በ2ኛ ደረጃ የሚቀመጥ ይሆናል ብለዋል፡፡ በ2036…

Read More

የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካው ሲጠናቀቅ በዓመት 30 ሚሊዮን ኩንታል የዩሪያ ማዳበሪያ የማምረት አቅም አለው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው። ማብራሪያ ከሰጡባቸው ጉዳዮች ውስጥ መንግሥት ዳንጎቴ ከተባለ የውጭ ድርጅት ጋር በመተባበር የሚያለማው የማዳበሪያ ፋብሪካ አንዱ ነው። ፋብሪካው በዓመት 30 ሚሊዮን ኩንታል የዩሪያ ማዳበሪያ የማምረት አቅም እንዳለውም ገልጸዋል። ፕሮጀክቱ ማዳበሪያን ከማምረት ባለፈ የሚመረተው ማዳበሪያ የአካባቢውን አፈር፣ የምርቱን አይነት እና…

Read More

ባንዳዎች ከጠላት ጋር በማበር ዓላማቸውን ለማሳካት የሚያደርጉት ጥረት ፈፅሞ አይሳካም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያን በቅጡ ያላወቁ የውስጥ ባንዳዎች ከጠላት ጋር በማበር ዓላማቸውን ለማሳካት የሚያደርጉት ጥረት ፈፅሞ ሊሳካ እንደማይችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰላም እና ፀጥታን በሚመለከት ለፓርላማው በሰጡት ማብራሪያ፣ የኢትዮጵያን ዕድገት የማይሹ ሀገራት በጦርነት እንደማያሸንፉን ስለሚያውቁ ያላቸው ምርጫ ባንዳዎችን መላክ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያን በቅጡ ያላወቁ የውስጥ ባንዳዎች ደግሞ ከጠላት ጋር በማበር ዓላማቸውን የሚያሳኩ እንደሚመስላቸው…

Read More

የባሌ ህዝብ የሀገርን ሀብት ጠብቆ በማቆየቱ መመስገን አለበት – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

የባሌ ህዝብ የሀገር ሀብት የሆኑትን ብሔራዊ ፓርክና የሶፍ ኡመር ዋሻ ጠብቆ በማቆየቱ መመስገን አለበት አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ለምክር ቤቱ አባላት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ በዚሁ ወቅት የምክር ቤት አባል የባሌን ህዝብ በመወከል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡትን የምስጋና…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ አዲሱን የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በተመለከተ ያነሷቸው ነጥቦች፡-

የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ የዲዛይን ስራ አልቋል፤ አማካሪ ተቀጥሯል። ፕሮጀክቱ ሳይጀመር ሙሉ በሙሉ አርሶ አደሮች ቦታቸውን ሲለቁ ኑሯቸው ሳይስተጓጎል አማራጭ ቤት እና የኑሮ ዘዬ እንዲከተሉ ሰፊና እጅግ የሚያኮራ ስራ ተሰርቷል። ኢትዮጵያ እስካሁን ባለው ሁኔታ ለውጪ በረራ የምትጠቀመው የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያን ነው፤ ይህ ደግሞ ወደ ሩቅ ስፍራዎች የሚጓዙ አውሮፕላኖች በቂ የሆነ ነዳጅ ጭነው ሊነሱ አያስችላቸውም። አሁን የመረጥነው…

Read More

የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ተጨባጭ ስኬት ያስመዘገበ መሆኑን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሡ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ በ2017 ዓ.ም ኢትዮጵያ ታላላቂ የታሪክ እጥፋቶችን ያሳየችበት ስኬታማ እንደነበር በመግለጽ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ብዝኃ ዘርፍን መሠረት አድርጎ የተነደፈዉ ፖሊሲ ኢትዮጵያን ወደላቀ ብልጽግና እያሸጋገረ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣…

Read More