NATIONAL NEWS
የዲጂታል ጤና አገልግሎቶችን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ጤንነቴ የሞባይል መተግበሪያ የኢፌድሪ ፕሬዝደንት ታዬ አስቃስላሴ በተገኙበት ይፋ ተደረገ
ጤና ሚኒስቴር “ጤንነቴ የሞባይል መተግበሪያን” በአዲስ አበባ የሳይንስ ሙዚየም በመካሄድ ላይ በሚገኘው የዲጂታል ጤና ኮንፈረንስ እና ኤግዚቢሽን የመክፈቻ መርሃግብር ላይ ይፋ አድርጓል። በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢትዮጲያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት፣ ታዬ አስቃስላሴ ጤንነቴ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ መሆኑን በመግለጽ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የተዘጋጀዉን የዲጂታል ጤና ኮንፈረንስ እና ኤግዚቢሽን በይፋ ከፍተዋል። መንግስት የጤናው ዘርፍን ለማሳደግ እየተሰሩ የሚገኙ…
የታሪክ ተመራማሪው ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) …
ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) የተወለዱት ከአባታቸው አቶ ዴሌቦ ሸለሞ እና ከእናታቸው አሹሬ ደከጉ ግንቦት 1930 ዓ.ም በሀዲያ ዞን በቀድሞው አጠራር በሶሮ አውራጃ በኩፋና ቀበሌ ያሮ በተባለው መንደር ነው፡፡ ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) ገና የ13 ዓመት ልጅ ሳሉ ነበር በአንድ ሳምንት ውስጥ እናትና አባታቸውን ያጡት፡፡ በወቅቱም ብዙ ችግር አጋጥሟቸው እንደነበርና ከሦስት ዓመት በኋላ በአንድ ዘመዳቸው እርዳታ ሆሳዕና ከተማ…
የመገጭ ግድብ የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)
የመገጭ መስኖ ልማት ፕሮጀክት የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ በጎንደር በነበረን ጉብኝት የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን የሥራ ሁኔታ ገምግመናል ብለዋል። ፕሮጀክቱ 870 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ÷ ሥራው ሲጠናቀቅ 17 ሺህ ሔክታር በመስኖ አቅርቦት ይሸፍናል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስረድተዋል፡፡ የፕሮጀክቱ…
ለጆሮ ህመም አጋላጭ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአንገት በላይ ሕክምና ስፔሻሊስት ሐኪም ኦሊያድ ታረቀኝ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ስለ ጆሮ ህመም መንስዔ እና መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ አብራርተዋል። የጆሮ ህመም ምንድን ነው? እንደ ዶክተር ኦሊያድ ገለጻ፤ በጆሮ አካባቢ ያሉ የአካል ክፍሎችን የሚያጠቁ ህመሞች የጆሮ ህመም ሊባሉ ይችላሉ። በሳይንሱ የውጨኛው፣ የመካከለኛው እና የውስጠኛው የጆሮ…
ዝክረ ሰሜን ዕዝ በማዕከላዊ ዕዝ
በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈፀመው ጥቃት አምስተኛ ዓመት መታሰቢያ ክብረ በዓል “እንዳይደገም፤ መቼም አንረሳውም” በሚል መሪ ሃሳብ በማዕከላዊ ዕዝ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች እየተከበረ ይገኛል። የመከላከያ ሠራዊት አባላት ክስተቱ እንዳይደገም የምናስብበት እና የተሠዉትን ሰማዕታትን የምናስታውስበት ቀን ነው ብለዋል። ክስተቱ መቼም ሊደገም የማይገባው መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል፡፡ በጀግንነት ሃገርን መጠበቅ በቅንነት ሕዝብን ማገልገል መለያው የሆነው መከላከያ ሠራዊት በሰንደቅ ዓላማ ስር…
በቀጣናው የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለሚደረጉ ጥረቶች ድጋፍ ይደረጋል -ኢጋድ
በቀጣናው የምግብ ዋስትናን፣ የግብርና ምርታማነት ለማረጋገጥ ለሚደረጉ ጥረቶች ድጋፍ እንደሚያደርግ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) አስታወቀ። የኢጋድ የመስኖ ስትራቴጂ ጥናት ማረጋገጫ ወርክሾፕ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ሲሆን በመድረኩ የቀጣናው አባል ሀገራት ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ። በኢጋድ የኢኮኖሚ ትብብር እና ቀጣናዊ ትስስር ዳይሬክተር ሞሄለዲን ኤልቶሀሚ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ቀጣናው ተደጋጋሚ ድርቅንና የውሃ አቅርቦት ችግሮችን እየተጋፈጠ…
የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሻሻል የተከናወኑ ተግባራት በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው – የዓለም ጤና ድርጅት
ኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን ለማስፋት ያከናወነቻቸው ተግባራት የሚደነቁና በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። በዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ቺሳካት እንዳሉት ኢትዮጵያ የዜጎቿን የጤና አገልግሎት ጥራት ተደራሽነት ለማስፋት ያከናወነችው ተግባር የሚደነቅና በተሞክሮነት የሚወሰድ ነው። ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ቺሳካት ለኢዜአ እንደተናገሩት ባለፉት ጥቂት ዓመታት ኢትዮጵያ…
የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ንግድን ለማሳለጥና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል – ምሁራን
የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ንግድን ለማሳለጥና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ ለስኬቱ በጋራ መስራት እንደሚገባ የጅማ እና አምቦ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የቀይ ባህር ጉዳይ ህጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልክዓ ምድራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ነው ብለን እናምናለን ማለታቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ ተዘግቶባት መኖር አትችልም፤ ለጎረቤቶቻችን መናገር የምንፈልገው ኢትዮጵያ…
አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሃይማኖት ተቋማት ሚና መጠናከር ወሳኝ ነው
አስተማማኝና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሃይማኖት ተቋማት እየተወጡ ያለውን ሚና ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀኃፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ገለጹ። የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ህብረት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው ጉባኤ ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ዛሬ በአርባ ምንጭ ከተማ መክሯል። በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ቀሲስ ታጋይ ታደለ፤ አስተማማኝና ዘላቂ ሰላምን…
