Trendings

የግብርና ሚኒስትር፣ የሰላም ሚኒስትር እና የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሹመቶች በምክር ቤት ጸደቀ

የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ፣ የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ እና የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቢኒያም ኤሮ ሹመቶች በምክር ቤት ጸድቀዋል። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው። ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የተሾሙት የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ እና የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ ሹመቶችን አፅድቋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን…

Read More

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የዓባይ ተፋሰስ ሀገራትን የጋራ ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ነው

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን እና የዓባይ ተፋሰስ ሀገራትን የጋራ ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ የኃይል ማመንጫ ግድቦች የውሃ አስተዳደር በዕውቀትና በከፍተኛ ኃላፊነት የሚመራ መሆኑንም ተናግረዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም የሀገራት መሪዎች፣ የቀጣናዊ፣ አሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት መመረቁ ይታወቃል። የውሃና…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጥቅምት እና ሕዳር ወር 2018 ዓ.ም ቁልፍ የሆኑ ተከታታይ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተግባራትን አከናውነዋል።

በደቡብ አፍሪካ አዘጋጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ምድር በተካሄደው የቡድን 20 አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ላይ በመታደም ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት አስገኝተዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉባኤው ላይ መሳተፍ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በማስጠበቅ የአፍሪካን የጋራ ድምጽ ለማጉላት ያስቻለ ነበር። ይህም የአህጉሪቱ ተጽዕኖ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ እየጎለበተ መምጣቱን ያረጋግጣል። የመስኖ ልማት ፕሮጀክት እና የቱሪዝም ልማት እንቅስቃሴን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር…

Read More

ብሔራዊ ጥቅም ካልተከበረ እንደ ሀገር መቀጠል አይቻልም – ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)

የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ብሔራዊ ጥቅሙን ማስጠበቅ ያልቻለ ሀገር እንደ ሀገረ መንግስት መቀጠል አይችልም አሉ፡፡ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ከፋና ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፥ ብሔራዊ ጥቅም ለሀገረ መንግስት አንዱ ወሳኝ አንጓ ነው፡፡ ብሔራዊ ጥቅም ካልተከበረ ሀገራዊ ክብር እንደማይኖር አንስተው፥ የባህር በር ጉዳይም ከሰላምና ደህንነት አንጻር የብሔራዊ ጥቅም…

Read More

ተረጂነት ታሪክ፣ አምራችነት መገለጫችን እንዲሆን የገጠር ሽግግር ላይ መሥራት አለብን፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

********* ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “በመደመር መንግሥት የዕይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በሰጡት ስልጠና ሽግግር፣ ትሥሥር በመደመር መንግሥት በሚለው ሀሳብ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በማብራሪያቸውም ሽግግር ትሥሥር በመደመር መንግሥት ውስጥ ሦስት ወሳኝ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር አንስተው፤ እነርሱም የመጀመሪያው መንደርደሪያ፣ ሁለተኛው መሻገሪያ እንዲሁም ሦስተኛው ደግሞ መስፈንጠሪያ ነው ብለዋል። የመንደርደሪያው ሀሳብ ዓላማው አቅምን ከችግር…

Read More

ባለፉት የለውጥ ዓመታት የኢንቨስትመንት ከባቢውን ምቹ ያደረጉ የማሻሻያ ተግባራት ተከናውነዋል

ባለፉት የለውጥ ዓመታት የኢንቨስትመንት ከባቢውን መቀየር ያስቻሉ በርካታ ስኬታማ ማሻሻያዎች መከናወናቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን(ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ ባለፉት ሰባት ዓመታት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዐቅም ለማሳደግ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተነድፎ ዓይነተ-ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ነው። ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ከሚያተኩርባቸው ዘርፎች አንዱ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ፍሰት በይበልጥ ማሳደግ መሆኑንም አስረድተዋል። በዚህም የኢንቨስትመንት ምኅዳሩን ለማሻሻል…

Read More

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 50ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ 1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ላይ ነው፡፡ ስትራቴጂው ለዜጎች አዳዲስ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ የቴክኖሎጂ አቅምን ለማሳደግና መሰረተ ልማቶቹን ለማስፋፋት፣ መልካም አስተዳደር ለማስፈንና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማፋጠን እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን በተሻለ መንገድ ማሳካትን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ምክር ቤቱም በስትራቴጂው…

Read More

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች እና መከላከያ ዘዴዎች፡-

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምንድን ነው? o የማርበርግ ቫይረስ በሽታ በወረርሽኝ መልክ የሚከሰት የደም መፍሰስና ትኩሳት ህመም ነው። o በሰዎችም ሆነ በሌሎች እንስሳት ላይ ይከሰታል። የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸው? ከአፍ፣ ከአፍንጫ ወይም ከቆዳ ሥር ደም መፍሰስ፤ ከፍተኛ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት እና ራስ ምታት፤ የጡንቻ እና ጀርባ ህመም፤ ማቅለሽለሽ፣ የሆድ ህመም እና ተቅማጥ፤ ደረት፣…

Read More

ኮፕ 32 ኢትዮጵያ ያላትን የቱሪዝም አቅም ለዓለም ለማሳየት የሚረዳ ትልቁ ጉባኤ ይሆናል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኮፕ 32ን በውጤታማነት ለማሠናዳት የሚያስችል አቅጣጫ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮፕ 32 ቁልፍ የዝግጅት ተግባራትን ለማቀናጀት ከሚያስችለው የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ውይይት አድርገዋል። ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ለማስተናገድ ያላትን ቁርጠኝነት በሚያመላክተው በዚህ ውይይት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውጤታማ ጉባኤን ለማሠናዳት የሚያስችሉ ሀሳቦች ላይ አቅጣጫ ሰጥተዋል። ኮፕ 32 ጉባኤን ለሀገር ግንባታ እና ለገጽታ ግንባታ…

Read More