የመደመር መንግሥት የብዝሃ ኢኮኖሚ እሳቤ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ተወዳዳሪ አልሚዎችን እያፈራ ነው -ሚኒስትር መላኩ አለበል
የመደመር መንግሥት የብዝሃ ኢኮኖሚ እሳቤ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ተወዳዳሪ አልሚዎችን እያፈራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ለኢዜአ እንደገለጹት መንግሥት ለኢንዱስትሪ ልማት የሰጠው ትኩረት ዘርፉ በእጅጉ እንዲነቃቃና እመርታዊ ለውጥ እንዲያመጣ አስችሏል። ለአብነትም የፖሊሲ ለውጥ፣ የስትራቴጂ እና የተቋማትን ቅንጅታዊ አሰራር የሚያጠናክሩ የማሻሻያ ስራዎችን ጠቅሰዋል። በማሻሻያዎቹ በመታገዝ የኢንዱስትሪ ምርታማነትን ለመጨመርና የአምራች ዘርፉን እድገት በቀጣይነት…
