Trendings

ኢትዮጵያና አሜሪካ የ1 ነጥብ 466 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ስምምነት ፈረሙ

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የ1 ነጥብ 466 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ለጤናው ዘርፍ ልማት ትብብር የሚውል የ1 ነጥብ 466 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አድርጓል። ድጋፉ ለአምስት ዓመት ለጤና ዘርፍ ዘላቂ ልማት እና የጋራ ኢንቨስትመንት ማጠናከሪያ ትብብር የሚውል ነው። የመግባቢያ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና በኢትዮጵያ…

Read More

በኢትዮጵያ ልዩነቶች በሀገር በቀል እሴቶች መፈታት አለባቸው የሚለው የመደመር መንግሥት ዕሳቤ ውጤት እያስመዘገበ ነው

በኢትዮጵያ የሀሳብ ልዩነቶች በሀገር በቀል እሴቶች መፈታት አለባቸው የሚለው የመደመር መንግሥት ዕሳቤ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ የመደመር መንግሥት ሰላምን ለማረጋገጥ በሰላማዊ መንገድ ብቻ የሚል ግልጽ አቋም አለው፡፡…

Read More

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት፡-

ዛሬ የኬንያ ፕሬዝደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ተቀብያለሁ። ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጥልቅ፣ ታሪካዊ እና ወንድማዊ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው። በውይይታችን የሁለትዮሽ ግንኚኙነታችንን በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ የተለዋወጥን ሲሆን ይኽም በሰላም እና መረጋጋት፣ ንግግር ብሎም በአፍሪካ መር መፍትሔዎች ላይ ያለንን የወል ጽኑ አቋም የሚያሳይ…

Read More

ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 መሳካት የቴክኖሎጂና ምርምር ሥራዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን

ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 መሳካት አጋዥ የቴክኖሎጂና የምርምር ሥራዎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መሳካቱን መግለጻቸው ይታወቃል። በተለይም በሕዝብ መገልገያ ዲጂታል መሠረተ ልማቶች ዝርጋታ ውጤታማ ሥራ መከናወኑን አንስተው፥ ኢትዮጵያ ወሳኝ በሚባል ደረጃ ከጥሬ ገንዘብ ግብይት ወደ ዲጂታል…

Read More

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ27 ቢሊየን ብር በላይ የብድር ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ27 ቢሊየን ብር በላይ የብድር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንዳሉት፤ አየር መንገዱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ቦታ ያለው እንዲሆን በማድረግ ረገድ የድርጅቱ ሰራተኞች ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ አየር መንገዱ ከዚህ በፊት ለሰራተኞቹ 1 ሺህ 200 ቤቶችን ገንብቶ…

Read More

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት መልእክት

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተጻፉት “መደመር” ፣ “የመደመር መንገድ”፣ “የመደመር ትውልድ” እና “የመደመር መንግሥት” መጻሕፍት ሰው ተኮር በሆነ የብዝሃ ኢኮኖሚ ጉዞ ኢትዮጵያን በአጠረ ጊዜ ውስጥ ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር አግዘዋል። በእነዚህ መጻሕፍት የተነሱ እሳቤዎች ከንድፈ ሃሳብ ባሻገር በተግባር የተገለጡና ለትውልዱ ብሩህ ተስፋን ያጎናጸፉ ናቸው። መጻሕፍቱ አሁን ከሕትመት ባሻገር በ Medemer መተግበሪያ አማካኝነት በድምጽ ተተርጉመው ቀርበዋል።…

Read More

ለኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ምስጋናዬን አቀርባለሁ – ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ

የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በትላንትናው ምሽት ለተበረከተላቸው ‘የኢትዮጵያ ታላቅ ክብር ኒሻን’ ለኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ምስጋና አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልእክት፤ በዓለም ላይ ካሉት ጥንታዊ እና ሀብታም ስልጣኔዎች አንዱ በሆነ ሀገር መከበር፤ እጅግ በጣም ኩራት የሚንጸባረቅበት ነው ብለዋል። ይህ ክብር ባለፉት ዓመታት አጋርነታችንን ለቀረጹ እና ላጠናከሩት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ህንዳውያን ነው…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት እያደገ የመጣውን ዘርፈ-ብዙ ግንኙነት ያሳያል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል እያደገ የመጣውን ዘርፈ-ብዙ ግንኙነት ማደግ ያሳያል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በተዘጋጀ የእራት ግብዣ ላይ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም፤ የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት፣ የሚጋሯቸውን ዕሴቶችና ያላቸው ትስስር እየዳበረ መሄዱን አንስተዋል። በዚህም መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ…

Read More

ኢትዮ-ህንድ

ኢትዮጵያና ህንድ ከሁለት ሺህ ዓመታት የተሻገረ ሁለንተናዊ ግንኙነት እንደነበራቸው የተለያዩ መዛግብት ያስረዳሉ። ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮም በርካታ የህንድ ተወላጆች ኢትዮጵያን የኑሮ ምርጫቸው እንዳደረጉ የሚያመለክቱ በርካታ ማሳያዎች አሉ። በአንደኛውና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መካከል በነበሩት ዓመታት በርከት ያሉ ሕንዳውያን በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች በንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው ቆይተዋል፡፡ በፈረንጆቹ 1948 ኢትዮጵያ ከህንድ ጋር መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመሰረተች…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በአድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኖሩ

የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በአድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል። የናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት የኢትዮዽያና ህንድን የቆየ ታሪካዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት የሚያሸጋግር ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የመላ ጥቁር ህዝቦች የነጻነት ተምሳሌት የሆነውን የአድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል። ኢትዮጵያ እና ህንድ በዲፕሎማሲ፣ በኢኮኖሚ፣ በባህል ግንኙነት የረጅም ጊዜ ታሪክ አላቸው።

Read More