Trendings

በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ለተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ብሔራዊ የጀግና አቀባበል ይደረግለታል – የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር

በፓሪስ በተካሄደው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ለተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ብሔራዊ የጀግና አቀባበል እንደሚደረግለት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ። አትሌቶች በውድድሩ የሚገባውን ተጋድሎ መፈጸማቸውን ገልጿል። ሚኒስቴሩ የኢትዮጵያን የኦሊምፒክ ተሳትፎ በማስመልከት መግለጫ አውጥቷል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1956 በሜልቦርን በተካሄደው 16ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች አንስቶ በአጠቃላይ 15 ጊዜ ተሳትፎ ማድረጓን ገልጿል። ከሜልቦርኑ በስተቀር ከኦሎምፒክ በ14ቱ የተሳትፎ መድረኮች ካለ ሜዳሊያ ተመልሳ አታውቅም…

Read More

2016 በጀት ዓመት የኢትዮጵያን ዕድገት ያስቀጠልንበት ዓመት ነው -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

2016 በጀት ዓመት የኢትዮጵያን ዕድገት ያስቀጠልንበት ዓመት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሆኑ አስፈጻሚ ተቋማት የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2017 ዕቅድ የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የተጠናቀቀው በጀት ዓመት በብዙ መልኩ ስኬት የተመዘገበበት ነበር ብለዋል። በዚህም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ እድገት ማስቀጠል ተችሏል ነው ያሉት። ለሰላም…

Read More

በሐምሌ ወር የሰለጠነ የሰው ሃይል ወደ አውሮፓ ሀገራት መላክ ተጀምሯል፦ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

በሐምሌ ወር የሰለጠነ የሰው ሃይል ወደ አውሮፓ ሀገራት መላክ መጀመሩን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ፡፡ ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ፤ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዕቅድ አፈፃፀም ተገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫዎች መቀመጣቸውን ገልጸዋል፡፡ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተገኙ ልምዶችን በመውሰድ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ሁሉም የዘርፉ ባለድርሻ አካላት የራሳቸውን ሚና በአግባቡ በመለየትና…

Read More

ስታርትአፖችን ማስተናገድ የሚያስችል ሥነ-ምሕዳር ለመገንባት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

ስታርትአፖችን በአግባቡ ማስተናገድ የሚያስችል ሥነ-ምሕዳር ለመገንባት በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡: በኢትዮጵያ የስታርትአፕ ሥነ-ምህዳርን ምቹ ለማድረግ እየተዘጋጀ ባለው ረቂቅ አዋጅ ዝርዝር ይዘት ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) እና የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ የስታርትአፕ ረቂቅ አዋጅ ለማዘጋጀት የሚያስችሉ ግብዓቶች…

Read More

የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ትግበራው የወጪ ንግድና ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታና ተወዳዳሪነትን የሚያሳድግ ነው

የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ትግበራው የወጪ ንግድና ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታና ተወዳዳሪነትን የሚያሳድግ መሆኑን የሞሃን ኩባንያ ሊቀ-መንበር እና የህንድ ቢዝነስ ፎረም ሊቀመንበር ማዩር ኮታሪ ተናገሩ። በኢትዮጵያ በተለያዩ የማምረቻ ዘርፎች ላይ የተሰማራው የሞሃን ኩባንያ ሊቀ-መንበር እና የህንድ ቢዝነስ ፎረም ሊቀመንበር ማዩር ኮታሪ፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ትግበራውን በተመለከተ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በፖሊሲ ተግበራው በመንግስት የተወሰደው እርምጃ ብዙዎች ሲጠብቁት የነበረ…

Read More

dvfd

በቀጣዮቹ ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ አንዳንድ አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይጠበቃል በቀጣዮቹ አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡ ኢንስቲትዩቱ በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች የዝናብ ስርጭቱ እየተጠናከረ እንደሚሔድ ገልጿል፡፡ የሚጠበቀው እርጥበት የመካከለኛ ጊዜ ሰብሎችን ለመዝራት ፣በተለያየ የእድገት…

Read More

በሰው መነገድና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀሎችን ለመከላከል በጋራ እየተሰራ ነው

በሰው መነገድና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀሎችን ለመከላከል በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ። ብሔራዊና ክልላዊ የፍልሰት ትብብር ጥምረት የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ ክንውንና ቀጣይ ትኩረት ላይ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በአዳማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በላይሁን ይርጋ በመድረኩ ላይ እንደገለፁት መደበኛ ባልሆነ መንገድ ከሀገር የሚወጡ ዜጎች ለተለያየ ሰብዓዊ መብት…

Read More

ከ550 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊቀርብ ነው

ለ2017 በጀት ዓመት ከ550 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለማፀደቅ ዝግጅት መደረጉን ገንዘብ ሚኒስቴር ገለጸ። የ2017 የፌዴራል መንግሥት በጀት 971 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ሆኖ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁ ይታወሳል። በጀቱ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ21 ነጥብ 1 በመቶ እድገት ያሳየ ነበር። ከዚህ ውስጥ ለመደበኛ በጀት 451 ነጥብ 3 ቢሊየን…

Read More

ሚኒስቴሩ ከቻይና የገጠር ልማት ፋውንዴሽን ጋር በትብብር ለመስራት ተፈራረመ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከቻይና የገጠር ልማት ፋውንዴሽን ጋር በተለያዩ መስኮች በትብብር መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ ስምምነቱ በ2ኛው ምዕራፍ የትብብር ማዕቀፍ በ7 ዋና ዋና የልማት መስኮች ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፥ ኢትዮጵያና ቻይና በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፍ ለዓመታት የዘለቀ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰዋል።…

Read More

ሕዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ ዕቅድን በአግባቡ መተግበር እንደሚገባ ተገለጸ

አማራ ክልልን ከነበረበት ሁኔታ የሚያሻግርና ሕዝብን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሥራ ለመተግበር ዕቅድን በኃላፊነት መፈጸም እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስገነዘቡ፡፡ የአማራ ክልል ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በተገኙበት የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡ በመድረኩም ክልሉን በተለያየ መስክ ለማሳደግና ከ2018 እስከ 2022 ዓ.ም የሚተገበር ፍኖተ-ካርታ ተዘጋጅቶ በየደረጃው ላለው አመራር…

Read More